በአንባቢዎቿ ዘንድ ከፍተኛ ተነባቢነትን እያገኘች የመጣችው የእኛ እና የእርሶ የሆነችው ቤስት ስፖርት መፅሔት ነገ እናንተም ጋር ስትደርስ ከሀገር ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ ስፍራ ላይ ጥሩ በመንቀሳቀስ እና ጎልም በማስቆጠር የሚታወቀውን የምንተስኖት አዳነን የእግር ኳስ ሕይወት የሚዳስስ ዘገባን ስናቀርብላችሁ በእዚያ ውስጥ ስለ ሁለገብ ተጨዋችነቱ እንደዚሁም ደግሞ ከኳስ ውጪ ስላለው ሕይወቱና ስለክለቡ ያናገርነው ሲሆን ከባህር ማዶ ደግሞ የአርሰናሉ ተደናቂ ተጨዋች አሌክሲስ ሳንቼዝ በእዚህ ዓመት የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለቡድኑ ደጋፊዎች ለማበርከት ስለመዘጋጀቱ፤ ስለስዊድናዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አለቃ ዝላታን ኢብራሂሞቪች፤ በምርጥ ተከላካይ ነቱ ሁሉንም እያስማማ ስላለው የቼልሲው ዴቪድ ሉዊስ፣ የሊቨርፑሉ አዳማ ላላና ከሰው ልጅ ፍጡርም በላይ ስለሆነበት የውድድር ኣመት፤ 100 ፐርሰንት ትክክለኛ መድፈኛ ነኝ ስለሚለው የአርሰናሉ ኦሊቪዮ ዥሩ የሚወዷቸው ዘገባዎችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፤ ቤስት ስፖርት መፅሔት ከእነዚህ ውጪም ሌሎች ምርጥ ዘገባዎች የሚኖሯት ሲሆን በመሀልም ገጿም የሁለት ምርጥ ተጨዋቾች ፖስተር አዘጋጅታሎታለች፤ ቤስት ስፖርት ነገ እንዳታማልጦት፡፡
አስተያየት ይስጡ