ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሃል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የ2017 ቶታል የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ 2 መክፈቻ ጨዋታ እንዲመራ በካፍ ተመርጧል፡፡ ካፍ ዛሬ የዳኞችን ስም ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ፡፡
በውድድሩ ላይ የሚገኘው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ አርቢተር ባምላክ ተሰማ በምድብ ሁለት ከሚገኙት መካከል አልጄሪያ ከዚምባቡዌ የሚያደርጉትን ጨዋታ የዕለት እሁድ ጨዋታ ይመራል፡፡ ጨዋታው በፍራንስቪል ከተማ በሚገኘው ፍራንስቪል ስታዲየም ይደረጋል፡፡ ባምላክ በካፍ የዳኞች ደረጃ ኤሊት ኤ ላይ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ አርቢትር ነው
አስተያየት ይስጡ