መነሻ ገጽ Uncategorized የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በ105 ሚሊየን ብር ጥገናና ጣሪያ የማልበስ ስራ ሊከናወንለት ነው
Uncategorized

የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በ105 ሚሊየን ብር ጥገናና ጣሪያ የማልበስ ስራ ሊከናወንለት ነው

አጋራ
አጋራ

የአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የትራክ ንጣፍ እና ጣሪያ ማልበስ ስራን ለማከናወን ስምምነት ተፈረመ።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የቻይናው ዙዋንግንሚን ኩባንያ ናቸው ስምምነቱን የተፈራረሙት።

የስታዲየሙን የትራክ ንጣፍ እና ጣሪያ ማልበስ ስራ 105 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ይሆናል።

ስራው በ18 ወራት ውስጥ እነደሚጠናቀቅም ተጠቁሟል።

ስታዲየሙ ከዚህም በተጨማሪ አጠቃላይ እድሳት እንደሚደረግለት ነው የቢሮው ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እና የኩባንያው ተወካይ ዋንግ ሁ ስምምነቱን ሲፈራረሙ የተገለፀው።

በጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ የተሰየመው ስታዲየሙ በተለያየ ጊዜ ጥገና እንዲደረግለት ጨረታ ቢወጣም በዲዛይን ጥራት ችግር በሚፈለገው ፍጥነት ሊታደስ አልቻለም።

የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ የጥገና ስራው ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ክትትልና ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...