መነሻ ገጽ Uncategorized ​በፕሪሜየር ሊጉ ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልድያ ከተማን ያስተናግዳል
Uncategorized

​በፕሪሜየር ሊጉ ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልድያ ከተማን ያስተናግዳል

አጋራ
አጋራ

በኘሪሜየር ሊጉ ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልድያ ከተማን ያስተናግዳል

18ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬና ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ ይደረጋል።

በሊጉ ያለፉት አምስት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ያልቻለው ደደቢት 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ወልዲያን ያስተናግዳል።

ደደቢት በሊጉ ከተደረጉ 17 ጨዋታዎች መካከል ሰባት አሸንፎ በሰባቱ አቻ የወጣ ሲሆን በ3 ጨዋታዎች ተሸንፏል።

ወልድያ ከተማ በበኩሉ በሊጉ ከኤሌክትሪክ ቀጥሎ በርካታ ጨዋታዎችን (9 ) አቻ የወጣ ክለብ ሲሆን፥ በሊጉ የደረጃ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛለ።

ጨዋታው ደደቢት ከመሪዎች ተርታ ላለመራቅ ወልድያ ደግሞ ደረጃውን ለማሻሻል የሚያደርግ ይሆናል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ 11 ሰዓት 30 ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ጊዮርጊስ ለአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ወደ ኮንጎ ስላመራ ለሌላ ቀን ተላልፏል።

ሊጉ እሁድ ቀጥሎ ስድስት ጨዋታዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን፥ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 9 ስዓት ከ30 ላይ ንግድ ባንክ ከጅማ ይገናኛሉ።

በተመሳሳይ ሰዓት ክልል ላይ አዳማ ከወላይታ ዲቻ፣ አርባምንጭ ከሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ።

አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ 11 ስዓት ከ30 በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገናኛሉ።

በሊጉ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ጎንደር ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ ፋሲል ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል።

በሁለቱ ቡድኖች የመጀመርያ ዙር ጨዋታ ፋሲል ከተማ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 ማሸነፍ ይታወሳል።

ፋሲል በሊጉ የመጀመርያ ዙር አስደናቂ ጉዞ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ቡና ሰርቪያውን አሰልጣኝ ኒቮሳ ቩሲሲቪችን ካሰናበተ ወዲህ በገዛኸኝ ከተማ እየተመራ ጥሩ ግስጋሴ ላይ ይገኛል፤ በደረጃ ሰንጠረዡም ከመሪዎች ተርታ መሰለፍ ችሏል።

የእሁዱ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች በደረጃ ሰንጠረዡ አንዳቸው ከሌላኛው ላለመራቅ የሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ይሆናል።

ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ35 ነጥብ ሲመራ ሲዳማ ቡና በ31፣ ደደቢትና ኢትዮጵያ ቡና በ28 ነጥብ ተከታዩቹን ደረጃ ይዘዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...