መነሻ ገጽ Uncategorized ​በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል
Uncategorized

​በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል

አጋራ
አጋራ

በ2017ቱ የዱባይ ማራቶን በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ድል ተጎናፅፈዋል።

በወንዶቹ ውድድር አትሌት ታምራት ሞላ በ2 ስአት ከ4 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በመግባት አሸንፏል።

አትሌት ታምራት ውድድሩን ያጠናቀቀበት ስአት በማራቶን ውድድር ፈጣን ስአት ካስመዘገቡ ሶስት ኢትዮጵያን አትሌቶች መካከል ያሰለፈው ሲሆን፥ በውድድሩ ታሪክ ዘጠነኛው ፈጣን ስአት መሆኑ ተገልጿል።

ታምራት በ2012 በዱባይ ተይዞ የነበረውን የማራቶን ሪከርድም በ13 ሰከንዶች ማሻሻል ችሏል።

ሙሌ ዋሲሁን እና ሲሳይ ለማ ተከታዩን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።ማርክ ኮሪር ሎክማዋናይ 5ኛ ደረጃን ከመያዙ ውጭ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አስደናቂ ውጤት አስመዝግበዋል።

በውድድሩ ትልቅ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶት የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን ለመስጠት በወጡበት የዱባይ ማራቶን በሴቶችም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 9ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረውታል።
አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ በ2 ስአት ከ22 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ውድድሩን አሸንፋለች። ሹሬ ደምሴ እና የብርጓል አራጌ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ከአራተኛ እስከ 9ኛ ያለውን ደረጃም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይዘው አጠናቀዋል።

በዱባይ ማራቶን የሚያሸንፉ አትሌቶች 200 ሺህ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...