በደቡብ ካስትል ሲቲ ካፕ ዋንጫ ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አሸንፎ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለ

image

የደቡብ ክለቦች ወደ ፕሪምየር ሊጉ ከማምራታቸው በፊት የራሳቸውን አቋም ለመለካት እንዲችሉ ክልላቸው የሚያዘጋጅላቸው የደቡብ ካስትል ካፕ ዋንጫ ዘንድሮም በሐዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን በሁለት ምድብ ተከፍሎ በተከናወኑ ግጥሚያዎችም ከምድብ አንድ ድሬዳዋ ከተማ ሐዋሳ ከተማን 2-1 በመርታትና ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር አቻ በመለያየት በ4 ነጥብ በአንደኝነት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ሲያልፍ ሐዋሳን 1-0 የረታው አርባምንጭ ደግሞ ብዙ ባገባ ተቀድሞ በተመሳሳይ 4 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ አልፏል፡፡
ከምድብ ሁለት በተደረገው ጨዋታም በተጋባዥነት የቀረበው ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 4-1 ወላይታ ድቻን 2-1 እና ፋሲል ከተማን 2-1 በመርታት በ9 ነጥብ ግማሽ ፍፃሜውን ቀደም ሲል መቀላቀሉን ሲያረጋግጥ ዛሬ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 3-2 ረትቶ በ6 ነጥብ የግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለ ሌላው ቡድን ሆኗል፡፡
የደቡብ ካስትል ካፕ ጥሩ ፉክክር እየተደረገበት ባለበት በአሁን ሰዓት የግማሽ ፍጻሜው ጨዋታም በድሬዳዋ ከተማ እና በሲዳማ ቡና እንደዚሁም ደግሞ በኢትዮጵያ ቡናና በአርባምንጭ ከተማ መካከል የሚከናወን ይሆናል፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook