መነሻ ገጽ Uncategorized በእግር ኳስ ተጫዋቾች በተደረገው የዕድሜ ማጣራት 65 በመቶ ምርመራውን ማለፍ አልቻሉም
Uncategorized

በእግር ኳስ ተጫዋቾች በተደረገው የዕድሜ ማጣራት 65 በመቶ ምርመራውን ማለፍ አልቻሉም

አጋራ
አጋራ

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ በተደረገው የዕድሜ ማጣራት 65 በመቶ ምርመራውን ማለፍ  አልቻሉም።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው ይህን ያስታወቀው።

በዚህ ዓመት ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች በሚገኙ በ2 ሺህ 10 የእግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ የዕድሜ ምርመራ ተደርጓል።

በምርመራው በትክክለኛ ዕድሜ የተገኙትና ምርመራውን ማለፍ የቻሉት 702 ተጫዋቾች ብቻ ሲሆኑ፥ 1 ሺህ 308ቱ ደግሞ ምርመራውን ማለፍ አልቻሉም።

982ቱ የመጀመሪያውን የተክለ ሰውነት ምርመራ ማለፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን 326ቱ የኤም አር አይ ምርመራ ማለፍ እንዳልቻሉ ተነግሯል።

ባለፉት ዓመታት በዕድሜ ማጭበርበር ምክንያት ብሄራዊ ቡድኑን የሚተኩ ተጫዋቾች ማግኘት አዳጋች እንደነበር የብሄራዊ ቡድን ሐኪምና በፌዴሬሽኑ የህክምና ኮሚቴ አባል ዶክተር አያሌው ጥላሁን ተናግረዋል።

አሁን ግን በዘመናዊ መሣሪያ የታገዘ ምርመራ መደረጉ ለብሄራዊ ቡድን ተተኪ ወጣቶች በትክክለኛ ዕድሜ መገኘታቸውን ነው የገለጹት።

በዕድሜ ማጣራት ስራው አብዛኞቹ ተጫዋቾች የልደት ሰርተፍኬት ማጭበርበር፣ መታወቂያ በሌላ ሰው ማሰራት እና የምርመራ ውጤትን ያለመቀበል ችግሮች መታየታቸውን ገልጸዋል።

አብዛኛዎቹ አሰልጣኞች ውጤት ከመፈለግ የተነሳ የዕድሜ ምርመራ እንዲደርግ እንዳማይፈልጉም ነው ዶክተር አያሌው የገለጹት።

የዕድሜ ማጣራት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ደግሞ በፌዴሬሽኑ የህክምና ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነስረዲን አብዱራሂም ናቸው።

በምርመራው ከ12 በላይ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች መሳተፋቸውና የምርመራ ስራው አዲስና ዘመናዊ መሆኑንም ተናግረዋል።

ፌዴሬሽኑ ቀጣይ በሚደረጉ ከ17ና ከ20 ዓመት በታች የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግና ያልተገባ ተጫዋች በሚያሰልፉ ክለቦች እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።

ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜሲካሄድ፤ ከ20 ዓመት በታች ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...