መነሻ ገጽ Uncategorized ​በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲቀናው መከላከያ ከ ኤሌትሪክ አቻ ተለያይቷል
Uncategorized

​በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲቀናው መከላከያ ከ ኤሌትሪክ አቻ ተለያይቷል

አጋራ
አጋራ


የሲቲ ካፑ  የምድብ ሀ ቡድኖች ዛሬም የሁለተኛ ጨዋታቸውን በ9 ሰዓት ሲያደርጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባቡና  ጋር ባደረጉት  ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴን አድርገው ቢወጡም ለቅዱስ ጊዮርጊስ የአሸናፊነትዋን ጎል በ 80ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር  ቡድኑን ወደ ግማሽ ፍፃሜ እንዲያልፍ ያደረገው ወጣቱ ተጨዋች  ⚽ አቡበከር ሳኒ ነው::
ልክ 11:05 ሲል የተጀመረው የመከላከያ  እና የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ጨዋታም ሁለቱ ቡድኖች ለመሸናነፍ ጥሩ ፉክክር ያደረጉበት ቢሆንም ጨዋታቸውን በ2-2 አቻ ውጤት ሊያጠናቅቁ ችለዋል፡፡ በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጎል በማግባት ቀዳሚ የሆኑት መከላከያዎች በ26ኛው ደቂቃ ላይ በ ⚽ ሳሙኤል ሳሊሶ አማካይነት ሲሆኑ ኢትዮ ኢሌክትሪኮች የአቻነቷን ግብ ⚽ በ  ኢብራሂም ፎፋና አማካኝነት በ43ኛው ደቂቃ ለማስቆጠር ችለዋል::
ከእረፍት መልስ ወደሜዳ ሲገቡም ጎል በማስቆጠር ቀዳሚ የነበሩት ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች ሲሆኑ የመሪነትዋን ጎልም ከዳዊት እስጢፋኖስ የተቀበለውን ኳስ በ61ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ⚽ዲዲየር ካቦሞባን ሲሆን ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተቃረበበት 82ደቂቃ ላይ ደግሞ መከላከያን ከሽንፈት የታደገችውን ⚽ ጎል የተሻ ግዛው አስቆጥሮ በአቻ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል::
ጨዋታዎቹ በነገው እለትም ሲቀጥሉ :-
ረቡእ ጥቅምት 16 ቀን 2009

09፡00 አዲስ አበባ ከተማ ከ ደደቢት

11፡00 አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታሉ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ካሌብ በየነ ወሳኙን ግብ አስቆጥሮ ሸገር ሲቲን የድል ሦስት ነጥብ አስጨበጠ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...

Uncategorized

“ግብ ጠባቂ ለኢትዮዽያ መምረጥ ከብዶናል” አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስብስቡ አራት ተጫዋቾችን ከስብስቡ ቀንሷል።

በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ...

Uncategorized

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ላይ ይደረጋል

ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ። የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል።...