መነሻ ገጽ Uncategorized በኘሪሜየር ሊጉ ደደቢትና ወልዲያ ድል ቀንቷቸዋል
Uncategorized

በኘሪሜየር ሊጉ ደደቢትና ወልዲያ ድል ቀንቷቸዋል

አጋራ
አጋራ

በ19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት እና ወልድያ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል።

ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ደደቢት 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ጌታነህ ከበደ በ18ኛው እና 42ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሽመክት ጉግሳ በ68ኛው ደቂቃ ለደደቢት የአሸናፊነት ግቦችን አስቆጥረዋል።

ሀዋሳ ከተማ  በ80ኛው ደቂቃ የተገኘችውን ፍፁም ቅጣት ምት በፍሬው ሰለሞን አማካኝነት አስቆጥሯል።።

በሼህ መሀመድ አሊ አል አሙዲ ስታዲየም መከላከያን ያስተናገደው ወልድያ ከተማ 1 ለ 0 አሸንፏል።

ብቸኛዋን ግብም ያሬድ ብርሃኑ በ23ኛው ደቂቃ ከመረብ አዋህዷል።

ጅማ ላይ ጅማ አባቡና ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ሶዶ ላይ ወላይታ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል።

በነገው እለት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9 ስአት ላይ የሚጫወት ሲሆን፥ በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ 11 ስአት ከ30 ላይ ድሬዳዋ ከተማን ያስተናግዳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...