ከኮንጎው ኤሲ ሊዮፓርድስ ጋር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
በዚህም በድምር ውጤት 3 ለ 0 በመርታት በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ የመጨረሻ 16 ቡድኖች ውስጥ መቀላቀሉን አረጋግጧል።
የማሸነፊያ ግቦቹንም ሳላዲን ሰይድ በ16ኛው እና በ91ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
- ማሰታውቂያ -
ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባቱን ተከትሎ 550 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያገኝ ይሆናል።
በ2017ቱ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የሲሸልሱን ኮቲዲኦር በደርሶ መልስ በመርታት ወደ ጥሎ ማለፉ የገባው ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ኤሲ ሊዮፓርድስን ባሳለፍነው ሳምንት በዶሊሴ ከተማ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።