የ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን በአንደኝነት እና በሁለተኝነት በማጠናቀቅ የአፍሪካ ቻምፕየንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋገጡት ሁለቱ ክለቦች ከደቂቃዎች በፊት በግብፅ ካይሮ በወጣ ድልድል የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል ።
በቻምፒየንስ ሊጉ የሚሳተፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅድመ ማጣሪያ ከሱዳኑ አል ሂላል የተደለደለ ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታውንም በሜዳው የሚያደርግ ይሆናል ።
የዚህ ጨዋታ አሸናፊ ከታንዛንያው ያንግ አፍሪካ እና የደቡብ ሱዳኑ ዛላን አሸናፊ የሚጫወት ይሆናል ።
በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ የሚሆነው ፋሲል ከነማ በበኩሉ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ የደረሰው ሲሆን ቀዳሚ ጨዋታውን በሜዳው የሚያደርግ ይሆናል ።
- ማሰታውቂያ -
የዚህ ጨዋታ አሸናፊ ከቱኒዚያው ሲኤስ ሴፋክሰን የሚጫወት ይሆናል ።
የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከጳጉሜ 4 – መስከረም 1 ባሉ ቀናት ሲደረጉ የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከመሰከረም 6 – መስከረም 8 ድረስ ይደረጋሉ ።