መነሻ ገጽ Uncategorized በቻን የማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን ይገጥማል
Uncategorized

በቻን የማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን ይገጥማል

አጋራ
አጋራ
   ኬንያ በ2018 በምታዘጋጀው የአፍሪካ አገሮች ሻምፒዮንሺፕ (ቻን) የማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር ይጫወታል። በአገር ውስጥ ሊግ ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በሚሳተፉበት የቻን ውድድር የተሳታፊ አገሮች የማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆኗል።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጀመሪያው ማጣሪያ ጨዋታ በመጪው ሐምሌ ከሜዳው ውጭ ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ይጫወታል።

የብሔራዊ ቡድኑ የመልስ ጨዋታ ደግሞ ከሳምንት በኋላ የሚደረግ ይሆናል። በደርሶ መልስ ያሸነፈው ቡድን ከቡሩንዲና ከሱዳና አሸናፊ ጋር እንደሚገናኝ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። በ2018 የቻን የማጣሪያ ውድድር ታንዛኒያ ከሩዋንዳ ጋር የምትጫወት ሲሆን ቡሩንዲ ደግሞ ከሱዳን ጋር ትገጥማለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአራተኛ ጊዜ በ2016 በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በተካሄደው ውድድር መሳተሱ የሚታወስ ነው። ዋልያዎቹ በምድብ ሁለት ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ከአንጎላና ካሜሩን ጋር ተደልድለው በሁለቱ ተሸንፈው በአንዱ ደግሞ አቻ ወጥተው በአንድ ነጥብ ብቻ በጊዜ ተሰናብተዋል።

ለ5ኛ ጊዜ በ2018 በሚካሄደው የቻን ውድድር 16 አገራት የሚሳተፉ ሲሆን ውድድሩ በኬንያ አስተናጋጅነት በሚቀጥለው ዓመት ጥር ላይ የሚደረግ ይሆናል። የቻን ውድድር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2009 ከተጀመረ ወዲህ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሁለት ጊዜ፣ ቱኒዚያና ሊቢያ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...