መነሻ ገጽ Uncategorized በቶታል 2017 የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ውድድር እየተሳተፈ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ላይ የመልስ ጨዋታውን ያካሂዳል።
Uncategorized

በቶታል 2017 የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ውድድር እየተሳተፈ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ላይ የመልስ ጨዋታውን ያካሂዳል።

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኮት ዲ ኦር የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም  ከ ቀኑ 10:00 ላይ ይደረጋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያ ጨዋታው ላይ ወደ ሲሺየልስ አቅንቶ በሳልሀዲን ሰዒድ ሁለት ጎሎች  ኮት ዲ ኦር አቻውን 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።በቅዱስ ጊዮርጊስ  እግር ኳስ ክለብ  በኩል በመልስ ጨዋታው ውጤቱ አስጠብቆ ለመውጣት እና  ዙር ወደ ቀጣዮ ለማለፍ መልኩ ዝግጅታቸውን እንደሚያደርጉ ታውቋል።አላስፈላጊ እንግልት እና ድካምን ለማስቀረት ወደ ሀዋሳ ቀደም ብለው  መጓዛቸውም ተገልፃል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚ የሲሺየልሱ ኮት ዲ ኦር እግር ኳስ ክለብ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኮት ዲ ኦር መካከል በሀዋሳ የሚደረገውን ጨዋታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፊዴሬሽንም የስታድየም መግቢያ ዋጋ ይፋ አድርጓል፡-

ትሪቡን 100ብር፣ ካታንጋ 20ብር፣ ዳፍ እና ሚስማር 10ብር መሆኑን አስታውቋል በተጨማሪም የመሀል የትሪቡን መቀመጫ 200 መቶ ወንበር የተዘጋጀ ሲሆን ለክብር እንግዶች እና ጥሪ ለተደረገላቸው ግለሰቦች እንደሆነም ተገፆዎል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...