ከሜዳ ውጭ 5 ለ 0 አሸንፎ ሰፊ እድል ይዞ የመጣው ብሄራዊ ቡድናችን 2 ለ 1 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል።
ለተመልካች ማራኪ የነበረው የመጀመሪያው አጋማሽ የኢትዮፕያ ብሄራዊ ቡድን ሙሉ ለሙሉ ብልጫ ወስዶ ተጫውቷል ሁለት ጎልም ማስቆጠር ችለዋል ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ ባሳዩበት ጨዋታ ብዙ ጎል የሚሆኑ ኳሶችን አባክነዋል ።በ27ኛው ደቂቃ ስራ ይግዛው በቀኝ መስመር ከፔናሊቲ ቦክስ ውጭ አስደናቂ ጎል አስቆጥራለች። ተጨማሪ ጎል ለማግባት ጫና ፈጥረው የተጫወተው ብሄራዊ ቡድናችን በ30ኛው ደቂቃ አልጋነሽ ካልሳ ቅጣት ምት አስቆጥራ ልዩነቱን ሁለት አድርጋለች።
በሁለተኛው አጋማሽ ብዙም ሳቢ ያልነበረው ጨዋታው በቡሩንዲ በኩል የታክቲክ ለውጥ በማድረግ ተጫዋቾችን መሀል ሜዳ ላይ ተደርድረው ኦፍ ሳይድ በማስገባት የጨዋታውን እንቅስቃሴ ለመገደብ ሞክረው ተሳክቶላቸዋል በ55 ደቂቃ ላይ ያገኙትን ቅጣት ምት ወደ ጎል ቀይረው ውጤቱን 2-1 ማድረግ ችለዋል ጨዋታውም በዛው ውጤት ተጠናቋል ።
አስተያየት ይስጡ