ስድስት ክለቦች በሁለት ምድብ ተከፍለው በሚወዳደሩበት ትግራይ ዋንጫ የክልሉ ክለቦች የሆኑት መቐለ ከተማ፣ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርሲቲ፣ሽረ እንዳስላሴ፣ደደቢት፣ ኣክሱም ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማን በተጋባዥነት ያስተናግዳል።
ትላንት 9 ሰዓት በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት የተሳታፊ ክለቦች ተወካዮችና የውድድሩ ኣዘጋጆች በተገኙበት በተካሄደው ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ላይ እንደተገለጸው ከስታድየም መግቢያ ከሚገኘው ገቢ 70% ለተሳታፊ ክለቦች(ከተጋባዡ ድሬዳዋ ውጪ) በተጫወቱት ጨዋታ መጠን እንደሚከፋፈል፣20% ለሽቶ ሚዲያ ፕሮዳክሽን፣10% ለትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንደሚሆን፤ በውድድሩ በተጋባዥነት ሚሳተፈው ድሬዳዋ ከተማ ከስታድየም መግቢያ ከሚገኘው ገቢ እንደማይካፈል ሆኖም የውድድሩ ኣሸናፊ ሚሆን ከሆነ ለውድድሩ ሚዘጋጀው ዋንጫ እና ሽልማት እንደሚወስድ ተገልጽዋል።
የውድድሩ ፎርማት በተመለከተ ከውድድሩ ኣዘጋጆች በሁለት ምድብ ተከፍለው እንዲጫወቱ የሚል ሃሳብ ሲያቀርቡ ደደቢት፣መቐለ፣ወልዋሎ እና ሓወልቲ ኣክሱም በፎርማቱ ሲስማሙ ሽረ እንዳስላሴ እና ድሬዳዋ ከተማ ስድስቱ ክለቦች በዙር ኣንድ ክለብ 5 ጨዋታዎችን እንዲያደርግ የሚል ሃሳብ ኣቅርበዋል፤ፎርማቱን ለመወሰን በተሰጠው ድምጽ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ይካሄድ ሚለው ከስድስት ድምጽ ኣራቱን በማግኘቱ በምድብ ተከፍሎ እንዲካሄድ ተወስኗል።
አስተያየት ይስጡ