መነሻ ገጽ Uncategorized ​በሀገራችን ብቸኛዋ ባለ ቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገ የሚያዚያ 25/2009 ዕትሟ ጋር ትጠብቃቹሀለች እንዳታመልጦ
Uncategorizedሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

​በሀገራችን ብቸኛዋ ባለ ቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገ የሚያዚያ 25/2009 ዕትሟ ጋር ትጠብቃቹሀለች እንዳታመልጦ

አጋራ
አጋራ

​በሀገራችን ብቸኛዋ ባለ ቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ በነገ የሚያዚያ 25/2009 ዕትሟ ከልዩ ዲዛይን ጋር
በርካታ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ አዳዲስና ያልተሰሙ ዘገባዎቿ
ጋር በእጅዎ ልትገባ ህትመቷን በማጠናቀቅ ላይ ናት፡፡ ከሀገር ውስጥ
“አሰልጣኝነት ስራዬ ነው፤ ከስራዬ ባለፈ ግን ጊዮርጊስ ተወልጄ ያደኩ
ያህል የሚሰማኝና ሁልጊዜም ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪክ ሲወራ
ወይም ሲፃፍ ፋሲል አሻራው አንድ ቦታ እንዲኖር አጥብቄ
እፈልጋለሁ…” የሚለው አመለ ሸጋው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ
በቻምፒዮንስ ሊጉ የምድብ ድልድል እና በዘንድሮው የኢትዮጵያ
ፕሪሚየር ሊግ ዙሪያ ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ጋር አስደሳች ቃለ-ምልልስ አድርጓል፡፡ ሌላኛው
የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ ክለብ የሆነው ሲዳማ ቡና ውስጥ
የተፈጠሩ አዳዲስ ዘገባዎችን ይዘናል፡፡ እንደዚሁም በቅርቡ በድንገት
ህይወታቸው ያለፈውና ብዙሀኑን የስፖርት ቤተሰቦች ያሳዛነውን
የቀድሞውን ዝነኛ ተጨዋች፣ አርቢትር እና ኮሚሽነር ከማል
ኢስማኤልን ዘክረናቸዋል፡፡ ከባህር ማዶ የነገውን የቻምፒዮንስ ሊግ
ትንቅንቅ፣ የአርሰናልን አጣብቂኝ ውስጥ መግባት፣ የኒውካስልን
ዳግም መመለስ፣ ስለ አርሰናል አዲሱ ፎርሜሽን፣ ስለ ቼልሲ የዋንጫ
ግስጋሴ እና በሌሎችም በርካታ የእንግሊዝ፣ የጣልያን እና የስፔን
ሊጎች ዙሪያ ከተሰሩ ዘገባዎች ጋር እንገናኛለን፡፡ በጉጉት
የምትጠብቁት የመዝናኛ ገፃችንም እንደ ተጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ
በተጨማሪም በፊት ለፊት የከለር ገፅ ዲዛይናችን ላይ አዲስ ለውጥ
አድርገናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ የሚወጡ አዳዲስ የሀገር
ውስጥ መረጃዎችን በድረ-ገፃችን www.hatricksport.com ላይ
መከታተል ይችላሉ፡፡ የነገ ዕለተ ረቡዕ ሚያዚያ 25/2009 የሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...