መነሻ ገጽ Uncategorized በኘሪሜየር ሊጉ ቅ/ጊዮርጊስ መሪነቱን አጠናክሯል
Uncategorized

በኘሪሜየር ሊጉ ቅ/ጊዮርጊስ መሪነቱን አጠናክሯል

አጋራ
አጋራ

በ26 ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የመጨረሻው የሳምንቱ ጨዋታ ዛሬ በ10 ሰአት በአዲስ አበባ ሲታዲየም የተደረገው የሊጉ መሪ ቅ/ጊዮርጊስ እና የሃዋሳ ከተማ   ጨዋታ  በቅ/ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

18254468_1710144059002868_1686226179_n

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱ ክለቦች የተመጣጠነ የኳስ ፍሰት የነበረው ጨዋታ ሲጫወቱ ነበር ገና ጨዋታው በተጀመረ በ4ኛው ደቂቃ የሃዋሳው  አጥቂ ጋዲሳ መብራቴ  በግራ በኩል  አጥብቦ የመታትን  የግቡ ቋሚ  መልሶበት ግብ ሳይሆን ቀርቷል ሃዋሳ ከተማዎች ሌላ የግብ ማግባት አጋጣሚ ለመፍጠር  20ደቂቃ መጠበቅ ነበረባቸው በ24ኛውደቂቃ ጋዲሳ መብራቱ   ከፍሬው ሰለሞን የተቀበለውን  ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ዘሪሁን መልሶበታል።  ቅ/ጊዮርጊስ በበኩሉ የጨዋታውን አብዛኛውን ደቂቃ  በራሳቸው ሜዳ ላይ ኳስን  ተቆጣጥሮ ለመጫወት ነበር የሞከሩት  አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት የግብ እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውለዋል ገና ጨዋታው በተጀመረ   በ5ኛው ደቂቃ  ሳላዲን  ሰኢድ ከበረኛ ጋር   ተገናኝቶ መጠቀም ያልቻለበት እንዲሁም  በ13ኛው ደቂቃ የግቡ አግዳሚ መልሶ ያወጣበት ለፈረሰኞቹ የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር ሆኖም  በ16ኛው ደቂቃ  ከኒክማ የተሻገረለትን ኳስ  የተከላካዮች  ስህተት ተጠቅሞ ሳላዲን በቀላሉ  በረኛውን በማለፍ የጨዋታውን ብቸኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

18280730_1710144025669538_760926672_n

የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 3ደቂቃ ሲቀረው ሳላዲን ከሃዋሳው በረኛ  ከሳሆሆ ጋር ተገናኝቶ  ሳሆሆ የመለሰበት ሌላው ተጠቃሽ የግብ ማግባት ሙከራ ነበር።

18217416_1710143355669605_597999712_n

በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመሪያውን 20ደቂቃዎች የሃዋሳ ከተማ ተጨዋቾች ኳስን ተቆጣጥረው የተሻለ ተንቀሳቅሰው ነበር ነገርግን ምንም አይነት የግብ   ማግባት ሙከራ የታከለበት   አልነበረም  ከ67ኛው ደቂቃ  ቡሃላ ግን ፈረሰኞቹ  አዳነ ግርማን በራምኬል ሎክ ፍሬዘር ካሳን በደጉ ደበበ እንዲሁም ምንተስኖት አዳነን በተስፋዬ አለባቸው ከቀየሩ ቡሃላ ጨዋታውን   ሙሉ በሙሉ  መቆጣጠር ችለዋል ሃዋሳ ከተማዎች መድሃኔ ታደሰ እና ፍርዳወቅ ሲሳይን  ወደሜዳ  ቀይረው ቢያስገቡም ውጤቱን መቀልበስ ግን አልቻሉም። በዚህም ቅ/ጊዮርጊስ  መሪነቱን ሲያጠናክር ከተከታዩ ሲዳማ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ልዩነቱን በ3 ነጥብ አድርሷል።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...