በሀገራችን ብቸኛዋ ባለ ቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ሀትሪክ ስፖርት የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ እትሟን ነገ ረቡዕ መስከረም 4/2009 ዓ.ም ማለዳ አዳዲስ ካልተሰሙ

 

የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎቿ ጋር በእጅዎ ትገባለች፤ ለመሆኑ ሀትሪክ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ትመጣ ይሆን?
ከሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የውል ጊዜ ሳያጠናቅቅ የፕሪምየር ሊጉን አዲስ መጪውን ጅማ አባቡናን የተቀላቀለው ቢኒያም አሰፋ ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ምን ብሎ ይሆን? ተጨዋቹ ክለቡን ስለለቀቀበት ምክንያት ይናገራል፤ ከደደቢት የተጨዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ ባለፈው ሐሙስ ፊርማውን ያኖረው ጌታነህ ከበደ ዝውውሩ ሳንካ እንደገጠመው መረጃው ደርሶናል፤ ተጨዋቹም ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል፤ ሌላው የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት አቶ አጥናፉ ዓለሙ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን በሳምንቱ መጨረሻ ከማሊ አቻው ጋር ባማኮ ላይ ስለሚያደርገው ጨዋታና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሉት ነገር አላቸው፡፡ ከአትሌቲክስ ጉዳዮች ጋር በተያያዘም ሀትሪክ ይዛ የምትወጣው ዘገባም አለና ሀትሪክ ጋዜጣ ነገ እንዳታመልጦት፡፡
ከባህር ማዶ፡- በማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ሰፋ ያለና ምርጥ የሆነ ዘገባ ቀርቧል፤ ከእዚያ ውጪ አንፊልድን ስላኮራው የሊቨርፑሉ ሮቤርቶ ፊርሚኖ፣ የዩናይትድ ደጋፊዎችን ቀልብ ስለገዛው ኤሪክ ባልይ ስለ አርሰናሉ ምርጥ ሳንቲ ካዞርላ እና በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የዛሬው ምሽት ጨዋታዎች የሚወዱት ሰፋፊ ዘገባዎች ቀርበዋል፡፡ የእንግሊዝ፣ ስፔን የጀርመንና የጣልያን ሊጎችን በተመለከተም አዳዲስ መረጃዎች አሉ፤ የመዝናኛ ገፅም በከለር አምሮና ደምቆ መጥቷል፡፡ ሀትሪክ ሁሌም የእርሶ ስለሆነች በፍፁም እንዳታመልጦት
ሌላም አዲስ ነገር አለ
ባለፈው ዓመት ሀትሪክ ስፖርትን በሀገራችን የመጀመሪያዋ ባለቀለም ጋዜጣ አድርገን ይዘን መቅረባችን የሚታወስ ነው፡፡ አሁንም በአዲሱ ዓመት ሌላ አዲስ ነገር ይዘን ልንመጣ ነው፡፡ ምን? ሀትሪክ ስፖርትን ከከተማ እስከ ገጠር፣ ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ በየትኛውም የዓለም ዳርቻ ሆነው በፈለጉት ጊዜና ሰዓት ገልጠው ለማንበብ ያስችሎት ዘንድ ራሷን ችላ በድረ-ገፅ ለመምጣት ዝግጅታችንን አጠናቅቀናል፡፡ በመሆኑም በአዲሱ ዓመት ሀትሪክ ስፖርትን በራሷ አዲስ ድረ-ገፅ ያገኟታል፡፡ www.hatricksport.com
ለማንኛውም የነገዋ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡

 

14305392_629111650590908_110526474185644112_o.jpg

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook