በሀገራችን ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት መፅሔት የሆነችው ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በኢሬቻ በዓል ላይ ህይወታቸው ባለፈው ወገኖቻችን የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ትመኛለች፡፡

በሀገራችን ብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት መፅሔት የሆነችው ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በኢሬቻ በዓል ላይ ህይወታቸው ባለፈው ወገኖቻችን የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ትመኛለች፡፡

ሀትሪክ ስፖርት በነገው የመስከረም 24/2009 ዓ.ም ዕትሟም እንደ ተለመደው ከበርካታ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች ጋር ከእጅዎ ለመግባት መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡ ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?

ከሀገር ውስጥ – አሰልጣኝ ደረጀ በላይ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ እና አስራት መገርሳ የክለቦቻቸውን የፕሪሚየር ሊግ ዝግጅት በተመለከተ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል፤ የሚናገሩት አላቸው፡፡

 

– የአመለ ሸጋውን ተጨዋች የሙሉጌታ ምህረትን የሽኝት ፕሮግራም በተመለከተ ዘገባ እና ሌሎችም መረጃዎች፡፡

 

ከባህር ማዶ- በማርከስ ራሽፎርድ፣ ቲዎ ዋልኮት፣ ሎሮ ኮስሌይኒ፣ ዲዬጎ ኮስታ፣ ጀምስ ሚልነር እና በሌሎችም ተጨዋቾች ዙሪያ ያጠነጠኑ ሰፋፊ ዘገባዎች፣ የስፔንና የጣልያን ሊጎችን የተመለከቱ መረጃዎች ካልተሰሙ የእግር ኳሱ ዓለም የመዝናኛ ወሬዎች ጋር ይዛላችሁ ቀርባለች፤ ይወዷታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ ዓመት ስራ በጀመረው ድረ-ገጿ www.hatricksport.com የተለያዩ የሀገር ቤት ስፖርታዊ መረጃዎችን ያገኙባታል፡፡ ነገ ማክሰኞ መስከረም 24/2009 ዓ.ም ከእጅዎ የምትገባው የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡ የነገ ሰው ይበለን፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook