መነሻ ገጽ Uncategorized ​ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል
Uncategorized

​ቅዱስ ጊዮርጊስ ደደቢትን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል

አጋራ
አጋራ

17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ የሳምንቱን ተጠባቂ አንድ ጨዋታን አስተናግዷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት የተደረገው ጨዋታ የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተከታዩ ደደቢት አገናኝቷል።

በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን ማጠናከር የሚችልበትን ድል አስመዝገቧል።ፈረሰኞቹ ጨዋታውን 3 ለ 2 ሲያሸንፉ፥

ሳልሃዲን ሰዒድ በ 15ኛ እና በ50ኛ በመጀመሪያው አጋማሽ እና በሁተኛው አጋማሽ 2 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

picsay-1485302969489

ምንተስኖት አዳነ ቀሪዋን  ጎል በ31ኛ ደቂቃ ላይ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሲያስቆጥር፥ ለደደቢት ጌታነህ

ከበደ በ71ኛ ደቂቃ  እና አበባው ቡጣቆ በ73ኛ ደቂቃ ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ35 ነጥብ መምራት ጀምሯል።

ተሸናፊው ደደቢት እና ሲዳማ ቡና ደግሞ በእኩል 28 ነጥቦች በጎል ክፍያ ተበላልጠው ይከተሉታል። ሌሎች ጨዋታዎች ነገ ሲካሄዱ፥ 9 ሰዓት

በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ። ሃዋሳ ላይ ሃዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ወልድያ ላይ ወልድያ ከተማ ከአርባ ምንጭ ሲጫወቱ ይርጋለም ላይ ደግሞ ሲዳማ ቡና ከአዳማ ከተማ ይገናኛሉ። ወላይታ ዲቻ በሶዶ ፋሲል ከተማን ሲያስተናግድ ጅማ ላይ ደግሞ ጅማ አባ ቡና ከአዲስ አበባ ከተማ ይጫወታሉ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ደግሞ 11 ሰዓት ከ30 ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ የሳምንቱን የመጨረሻ የሊጉን መርሃ ግብር ያከናውናሉ።

የደረጃ ሰንጠረዥ እና ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችን ይመልከቱ

 



ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...