“ሳላሀዲን ብቻ ሣይሆን እኛም እንደተመታን ነው የቆጠርነው…”ምንተስኖት አዳነ/የቅዱስ ጊየርጊስ አምበል/ ክፍል 2

“ሳላሀዲን ብቻ ሣይሆን እኛም እንደተመታን ነው የቆጠርነው…”

“የኮሮና ቫይረስን መመለስ የሚቻለው በፀሎት ብቻ ይመስለኛል”

“በገዛ ሜዳህ በደጋፊህ… ክልል ስትሄድ ደግሞ በተጋጣሚ ደጋፊ ጫና ውስጥ ሆነህ ውጤት መጠበቅ ይቻላል?”

ምንተስኖት አዳነ/የቅዱስ ጊየርጊስ አምበል/


ምንተስኖት፡- /ሳቅ በሳቅ../ አልቀበልም ይሄ ቀልድ ይመስለኛል፡፡ ፋብሪጋዝኮ የአርሰናልን፣ የቼልሲና የባርሴሎናንን ማሊያኮ ስሟል፡፡ እንደውም ተጨዋቹ የሚስመው ብሩን ነው ብዬ አምናለሁ …ማሊያ ሳመና
ክለቡን ይወዳል ብዬ አልቀበልም/ሳቅ/

ሀትሪክ፡- መጠጥ፣ ጫት… ሌሎች ሱሶች.. ለእግር ኳስ ተጨዋች አስጊ አይደለም?
ምንተስኖት፡- ምንም ጥያቄ የለውም.. እግር ኳስ ከሚከለክለው መታቀብ አለብን፡፡ በግሌ ካላስፈላጊና አጓጉል ከሆኑ ነገሮች ንፁህ ነኝ ተጨዋች ስለሆንኩ ሳይሆን በቃ ስለማልፈልግና ስለማይጠቅምም ነው
በእምነትም ይሁን ከጤና አንፃር ስታየው አያስኬድም… የተጨዋችነት ዘመን ቢበዛና ከበርታህ ከ20 አመት አይበልጥም በእነኚህ አመታት ደግሞ ብዙ ነገሮች ሊፈጠሩ ይችላሉና ያሰብካቸውን አመታትን ለመጫወት ካሰብክ
ራስን መጠበቅ የግድ ነው… በተለይ ከሱስ መቆጠብ በደንብ እረፍት ማድረግን ይጠይቃል ባይ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡-በቅዱስ ጊዮርጊስ ማሊያ የጨዋታ ዘመንህ የመጨረስ ህልም አለህ?

ምንተስኖት፡- የምመኘው እንደዚያ ነው…. የሌላ ክለብ ማሊያ ባልለብስ ደስ ይለኛል፡፡ በጊዮርጊስ ማሊያ የጨዋታ ዘመኔን ባቆም እመርጣለሁ፡፡ ዘንድርኮ 12ኛ አመቴን ይዣለሁ… ሲ ቡድን ላይ 2 አመት ዋናው
ቡድን ላይ ደግሞ 10 አመቴን ይዣለሁ… ከዚህም በኋላ በእግር ኳሱ ውስጥ ብዙ የመቆየት አላማ የለኝም፡፡ አቅሜን ስመለከተው ብዙ አመት እንደውም እስከ 10 አመት ድረስ ልጫወት እችላለሁ እዚያ መድረስ ግን
አልፈልግም ቶሎ ማቆምን እመርጣለሁ፡፡

ሀትሪክ፡-ምንቴ ብዙ የመረረህ ነገር ያለ ይመስላል ?

ምንተስኖት፡- /ሳቅ/ ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮች ኳሱ ውስጥ ታገኛለህ.. ደስ የሚሉ ነገሮች መኖራቸው ሳይረሳ….የትኛውም ሙያ ላይ ቻሌንጆች አሉ… እግር ኳስ ላይ መኖር ከምፈልገው ህይወት አንፃር ብዙ
የማይስማሙ ነገሮች አሉት በግሌ ብዙ ነገሮች አይመቹኝምና ቶሎ ብወጣ ደስ ይለኛል፡፡ በጊዮርጊስ ማሊያ ዘመኔን ቶሎ ብጨርስ ደስ ይለኛል፡፡

ሀትሪክ፡-እንደ አምበልነትህ የተጋጣሚ ቡድን ደረጃና የሌሎች ጨዋታ ውጤት የመከ ታተሉ ነገር ላይ ጎበዝ ነህ አሉኝ… አምበል ስለሆንክ ይሆን?

ምንተስኖት፡- አምበል ስለሆንኩ ብቻ ሣይሆን መረጃ የማየት ልምድ አለኝ፡፡ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ደግሞ መረጃዎች ይወጣሉ.. ይህን እከታተላለሁ፡፡ በተለይ በድረ ገጾች ላይ ሙሉ መረጃ ሲለቀቅ አያለሁ፡፡
ኃላፊነቴ ደግሞ ያስገድደኛል ብዙ መረጃዎችን አይቼ ስለተጋጣሚ ያለውን እውነት በመሰብሰብ ለቡድኑ አሰልጣኞች መረጃ የመስጠት ባህል አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ መረጃ ተከታትሎ ሙሉ ሆኖ መገኘት የቆየ ባህሪዬ ነው፡፡

ሀትሪክ፡- በአን ድ ቦታ ላይ ብቻ አለመጫወትህ እድገትህ ላይ ተፅዕኖ አልፈጠ ረብህም?

ምንተስኖት፡- ከበረኛ በስተቀር ሁሉም የሜዳ ክፍል ላይ ተጫውቻለሁ የመጀመሪያ ጨዋታ በጊዮርጊስ ማሊያ ያደረ ኩት በሚቾ ጊዜ ነው… ታች እያለውም የተከላካይ አማካይ ነበርኩ የምወደው ቦታም ያንን ነው ወደ
ዋናው ቡድን ሳድግም ረጅም ጊዜ የተጫወትኩት በዚህ ቦታ ላይ ነበር አሰልጣኞች ሲቀያየሩ የ የራሣቸው ሃሣብ አላቸው…. ያንን ማክበር ነበረብኝ አክብሬያለሁ፡፡ የማልረሳውም በአንድ ጨዋታ ላይ የገጠመኝ ነገር ነው…
በዚህ ጨዋታ ላይ ተከላካይ ሆኜ ገባሁ ከዚያ ግብ እንቢ ሲል አማካይ ሆንኩ.. ረጅም ሰዓት ግብ ሲጠፋ አጥቂ ሆንኩና እድለኛ ሆኜ ግብ አገባሁ… የሚገርመው ተመልሰህ ተከላክል ተብዬ ተከላካይ ሆኛለሁ፡፡ ይህን
አልረሳውም በእርግጥ አንድ ቦታ ላይ አለመጫወቴማ ተፅዕኖ አለው… ብዙም ነገር አጥቼበታለሁ ግን ደግሞ ክለቤ የሚለኝን ማድረጌ የግድ በመሆኑ አልተከፋሁም፡፡

ሀትሪክ፡-ከአባይ ግድብ ጋር ተያይዞ የግብጾችን ድንፋታ እንዴት አየኸው?

ምንተስኖት፡- አዎ ሰሞኑን ውዝግብ ነበርና በተለያየ ሚዲያ ስከታተል እንደነበረው ግድቡ ልዩነትን ፈጥሯል፡፡ ሠላም አውርደው ሀገራችንን በሚጠቅም መንገድ ላይ ተስማምተው ግድቡ ተገድቦ እናያለን ብዬ አስባለው፡፡
ጦርነት ባይኖር ደስ ይለኛል ቢሰማሙ እመርጣለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- የእግር ኳስ በቀልስ አያስፈልገ ንም ትላለህ?

ምንተስኖት፡- /ሳቅ በሳቅ/ አሁን ላይ ምንም መናገር አይቻልም ግልፅ ያለ ነገርም የለም፡፡ በኳሱ በርግጥ ግብፅም የበላይ ናት ይህን ማመን አለብን፡፡ ከተሰራ ግን ለውጥ እንዲመጣ አምናለው፡፡ ታላላቅ የአለማችን
ሊጎች ላይ በመጫወት ይበልጡናል፡፡ በርግጥ ኳሱ ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡ ያም ቢሆን ግብፅን ማሸነፍ ደስ ይላል እንደተጨዋች የተሻለ ነገር ሰርተን እንደምንለወጥ ተስፋ አደርጋሁ፡፡
በሊግ ደረጃ የግብፅ ሊግ ከኛ ይሻላል ከሰራንና ከበረታን በሊግም ሆነ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የማንበልጥበት ምክንያት ግን የለም፡፡ ሰርተውና ኳስ ላይ ትኩረት አድርገው ካደጉ እኛም መለወጥ እንችላለን ብዬ አምናለሁ፡፡
ዛማሊክእና ኢ.ኤን.ፒ.ፒ አይን ጨምሮ ብዙ የግብፅ ክለቦችን በሻምፒዮንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ካፕ ገጥሜ አይቻቸዋለው… ከትልቁ ክለብ ዛማሊክ ጋር በደርሶ መልስ ተጫውተን የተሸነፍነው እድለኛ ስላልነበርን ነውና
ከበረታን ማደግ እንችላለን እነርሱ እየሰሩ እያደጉ እየተለወጡ ሲመጡ እኛ ሀገር ግን በአንድ አጋጣሚ አንድ ውጤት ይመጣና ይቆማል አንቀጥምልበትም… በተቻለ መጠን ጠንክረን ከሰራን ግን የተሻልን መሆን እንችላለን፡፡

ሀትሪክ፡-ለኢትዮጵያ ምን ትመኛ ለህ?

ምንተስኖት፡- ደጋግሜ ተናግሬ የለሁ… ለኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ነገር እመኛለሁ ማለት አልፈልግም ሚዲያ ላይ ቀርቤ የማቀርበው ምኞትም ምንም አይጠቅምም… የሚጠቅመው ለፈጣሪ መማፀን መፀለይ
ሀገራችን ሠላም እንድትሆን አምላክን መለመን ነው የሚያዋጣው… ብዙዎች ብዙ ብለዋልኮ… ግን መፍትሔ አልመጣም ለችግሩ መፍትሔ ከራስ አለመጀመር ይመስለኛል፡፡ የግል ሠላም የሌለው ሰው ለኢትዮጵያ ሠላም
ማሰብ አለበት ብዬ አላስብም፡፡ መጀመሪያ ቅን መሆን ከቻልን ራስ ወዳድነታችን ካስቀረን ከዚያ በኋላ ፈጣሪን ብንለምንኮ ይሰማናል፡፡ ዋናው ሁሉም በእምነቱ ለፈጣሪ ተመችቶ መኖር ከቻለ ሀገሪቱ ሠላም ትሆናለች ሌላ
ምንም አያስፈልግም /ሳቅ/

ሀትሪክ፡-ፌስቡክ ትጠቀማለህ?

ምንተስኖት፡- በፊት የነበረኝን ዘግቻለሁ.. አሁን ምንም አይጠቅመኝም.. የሚሰሙትና የሚታዩት በሙሉ ደስ የማይሉና የሚረብሹ ናቸው… ዳግም መክፈትም አልፈልግም፡፡

ሀትሪክ፡-ባለፉት 10 የእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመንህ ፕሮፌሽናል የመሆን ፍላጎት ነበረህ?

ምንተስኖት፡- ሲጀመር ኳስ ተጨዋች እሆናለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም ፍላጎትም አልነበረኝም ብዙ ተጨዋቾች ሲጠየቁ ለፍተን ብዙ ዋጋ ከፍለን ነው ለዚህ የበቃነው ይላሉ… እኔ ግን ኳስ ተጨዋች ለመሆን ለፍቼ
አላውቅም… መክሊቴ ነው ብዬ አስ ቤም አላውቅም፡፡ ከዚህ አንፃር እግር ኳስ ተጨዋች ከሆንኩም በኋላ ፕሮፌሽናል ለመሆን ፍላጎቱንም አልነበረኝም ለመሆንም አልሞክርኩም፡፡

ሀትሪክ፡-አገባህ… ወይስ የፍቅር ህይወት ህ ምን ይመስላል?

ምንተስኖት፡- አላገባሁም… ደግሞም ቆሜ አልቀርም /ሳቅ በሳቅ/ ለአሁኑ የፍቅር ጓደኛ የለኝም፡፡ ከኔ ጋር የተጫወቱ ከኔ ጋር የተማሩ ከእኔ ጋርም ያደጉ አብዛኛው ወይ ያገባ … አግብቶም የወለደ ..
አግብቶም የፈታ አለ… ሁለተኛም ያገባ አለ /ሳቅ/ ምን ቀረህ ለምን አታገባም የሚሉ ሰዎች ያጋጥሙኛል ገንዘብ ካለህ ትዳር መያዝ ይቻላል ብለው የሚያስቡ አሉ ይሄ ልክ አይደለም… ከባድ ነው…. ትዳር ዝም ተብሎ
አይገባበትም ትልቅ የአዕምሮ ዝግጅትና ቁርጠኝነት ይፈልጋል… ለማንኛውም ጊዜው ሲፈቅድ ትዳር የምመሰርት ይሆናል /ሳቅ/

ሀትሪክ፡- .. የመጨረሻ ቃል.. ?

ምንተስኖት፡- ለዚህች ቀን ያደረሰኝ በእድሜና በጤና የጠበቀኝ እግዚብሔር ይመስገን… እናቱ እመብርሃንን ትመሰገን፡፡ ለዚህ ያበቁኝ ቤተሰቦቼ ናቸው እነሱን አመሰግናለሁ፡፡ አሁን ገባ የተባለው የኮሮና ቫይረስ
ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ጥንቃቄ ያስፈልገናል፡፡ ለሀገር ለሁሉም መፀለይ ይጠበቅብናል ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችም ሙሉ ድጋፋቸው አይለየን ከጎናችን ሁኑ ጭንቀታችሁ ይገባናል፡፡ ደስተኛ የሚያደርጋችሁ ውጤት
አስመዝግበን እንደም ናስጨፍራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ እናንተ ግን የሚፈለገው ውጤት እንዲገኝ እስከመጨረሻ ድረስ ድጋፋችሁ አይለየን ማለት እፈልጋለሁ አመሰግናለሁ፡፡


ክፍል አንድን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ 👇

“ሳላሀዲን ብቻ ሣይሆን እኛም እንደተመታን ነው የቆጠርነው…”ምንተስኖት አዳነ/የቅዱስ ጊየርጊስ አምበል/ ክፍል 1

 

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport