መነሻ ገጽ መከላከያ ​ሪፖርት | ወልዋሎ አዲግራት የሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ መከላከያ  የመጀመሪያ ድሉን አስመስግቧል
መከላከያሪፖርትወልዲያ

​ሪፖርት | ወልዋሎ አዲግራት የሊጉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ መከላከያ  የመጀመሪያ ድሉን አስመስግቧል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል መከላከያን ያስተናገዱት ወልዋሎ አዲግራት ከ1ዓመት በኃላ በሜዳቸው የ1-0 ሽንፈትን በመከላከያ  አስተናግደዋል፡፡

በጨዋታው መጀመርያ ወልዋሎዎች  4-3-3  አሰላለፍ  ይዘው  የገቡ  ሲሆኑ በአንፃሩ    በመከላከያዎች 4-5-1 አሰላለፍ ይዘው  ወደ ሜዳ ገብተዋል     ከመጀመርያው  45  የመጀመርያ የጨዋታ ክፍለ ግዜ  መከላከል መርጠው የተጫወቱ   መከላከያዎቹ  ሲሆኑ ወልዋሎዋች በአንፃሩ በኳስ ቁጥጥር ብልጫው ነበራቸው፡፡

በ 33ኛ ደቂቃ ላይ አማኑኤል ተሾመ በቀኝ መስመር የላካትን ኳስ የወልዋሎው ግብ ጠባቂ ዘውዱ መስፍን  እና ተከላካዮ በረከት የፈጠሩት ያለመግባባት ተጠቅሞ ምንይሉ ወንድሙ አስቆጥሮ ጦሩን ቀዳሚ አድርጎ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
ከእረፍት  መልስ  ከነጉዳቱ  ተሰልፎ የነበረው  አፍወርቅ  ሃይሉ አስወጥተው    ብሩክ አየለ ቀይረው  ጨዋታውን የጀመሩት ወልዋሎዎች  የተደራጀውን  የመከላከያዎች   የተከላካይ መስመርና   ጥሩ የነበረው  በረኛቸው  አቤል ማሞ  መስመር ሰብረው   ማለፍ  ሳይችሉ ሊሸነፍ ተገደዋል፡፡

በእለቱ  በወልዋሎዎች  ጥሩ የነበረው    እንየው ካሳሁንና የመከላከያው ሳሚኤል ሳሊሶ  እርስ በርስ በመጣለት የተጋጩ ሲሆን ሁለቱም በቀይ  ካርድ  ከሜዳ  ተወግደዋል፡፡

በሁለቱም በኩል 6ቢጫ የካርድች ተመዘዋል፡፡

ባጠቃላይ  በሁለቱም 45ደቂቃዎች  በመከላከሉም በመሃል  ክፍሉም  መከላከያዎች የተሻሉና የመናበብ    ጥሩ የስነልቦና  ቅንጅት  የነበራቸው  ሲሆኑ  ባንፃሩ ለመከላከያ  አጨዋወት በሚመች መልኩ  ረጅም  ኳስ ሲጫወቱ የነበሩት  ወልዋሎዎች  ከወትሮው  ወርደው  ታይተዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት 

 ብርሃነ ገብረእግዚአብሔር -ወልዋሎ አዲግራት

“እነሱ  አሸንፈውናል  በራሳችን  ስህተት በፈጠርነው አጋጣሚ  ተጠቅመዋል፡፡    እንጂ  በኳስ ቁጥጥር እኛ  የተሻልን ነበርን፡፡  ቀድመው  ግብ  ስላስቆጠሩብን  ስሜታዊ ሆነን በመግባታችን  ተረጋግተን  መጫወት አልቻልንም፡፡  በዚህም  ልንሸነፍ ተገደናል  በመሃል ክፍልም ተበልጠን  ነበር::”

ሻምበል ምንያምር ፀጋየ-መከላከያ

ከወልዋሎ  ያገኘነው   እንደ 3ነጥብ ሳይሆን  እንደ 6ነጥብ ነው  እምናየው  ወልዋሎ  አዲስ ክለብ  አይመስልም ፡፡    ወደዚህ የመጣነው  ሁለት  አላማ  ይዘን ነበር ከቻልን  ማሸነፍ  ካልቻልን   አቻ ለመውጣት  ነበር ፡፡የመጀመርያው  እቅዳችን  አሳክተናል   ስለ ደጋፊው  ቃላት ያጥረኛል  ደጋፊው   ገና ከመግባታችን  ጥሩ  አቀባበል  አድርጎልናል  በሜዳም  በሚገባና በስርአት ኳስ ለተጫወተ  ይደግፋል   ቡና ስንጠጣ  እንኳን ማን  እንደሚከፍለው  አናቀውም ነበር እናመሰግናለን”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

አህመድ ረሽድ (ሽሪላዉ) ወደ መከላከያ አምርቷል !!

  በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ በርካታ አዳዲስ...

መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

አምሳሉ ጥላሁን ሳኛ ወደ መከላከያ አምርቷል !!

  አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በዋና አሰልጣኝነት ከሾሙ በኋላ በዝዉዉር ገበያዉ በንቃት በመሳተፍ...

መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

መከላከያ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በኃላፊነት ሾሟል

ከተከፈተ 8ኛ ቀኑን በያዘው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ራሱን እያጠናከረ ያለው መከላከያ አሰልጣኝ...