አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ዋና አሰልጣኝ አድርገዉ ከሾሙ በኋላ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመንቀሳቀስ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት መከላከያዎች አሁን ደግሞ ግዙፉን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀል ችለዋል።
ከዚህ ቀደም ለወልደያ ከነማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ያለፉትን ሁለት አመታት ደግሞ በሀድያ ሆሳዕና ቤት ማሳለፍ የቻለዉ የተከላካይ አማካዩ ተስፋየ አለባቸዉ (ቆቦ) ሁለት አመት በሚቆይ ዉል ለመከላከያ መፈረሙ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ