በ2014 የውድድር ዓመት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመጨረሻ ቀን ከመውረድ የተረፉት ድሬዳዋ ከተማዎች ከቀናት በፊት ዮርዳኖስ ዓባይን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው ከሾሙ በኋላ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ሁለት ፈራሚዎቻቸውን ይፋ አድርገዋል ።
ሁለቱም ፈራሚዎች የወድድር ዓመቱን በአዲስ አበባ ከተማ ተጫውተው ማሳለፍ የቻሉት ግብ ጠባቂው ዳንኤል ተሾመ እና አማካዩ ኤልያስ አህመድ ሲሆኑ በምስራቁ ክለብ ለሁለት ዓመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ተፈራርመዋል ።
ዳንኤል ተሾመ ለአዲስ አበባ ከተማ ከመጫወቱ በፊት በወሊሶ ከተማ ፤ በሀምበሪቾ ዱራሜ እና በአዳማ ከተማ በአስተማማኝ ሁኔታ የግብ ዘብ ሆኖ ያሳለፈ ሲሆን ኤልያስ አህመድ በበኩሉ በባህርዳር ከተማ ፤ በጅማ አባጅፋር ፤ በወላይታ ድቻ እና በአዳማ ከተማ ተጫውቶ ማሳለፍ ችሏል ።