“የዳኝነት ስህተት በእግርኳሱ የሚያጋጥም ነው መነጋገሪያ ማድረግም አይገባም”
ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን
“ትልልቅ ሰዎች ያሉበት ጠንካራ ስራ የሚሰራበት እንዴት የኢትዮጵያ ስፖርት ይደግ የሚል እሳቤ ያላቸው መሪዎች በመኖራቸው ተደስቻለሁ”
ዶ/ር ሰይፉ ጌታሁን
/ የቦርድ ሰብሳቢ/
- ማሰታውቂያ -
“በመቻል የኢትዮጵያን ስፖርት ታሪክ እንቀይራለን ብዬ አምናለሁ ያንንም ለማድረግ እየሰራን ነው ነገር ግን የማያሰራ ነገር ካለ ጥለን ነው የምንሄደው”
አቶ ጸሃዬ ሽፈራው
/የቦርዱ ም/ል ሰብሳቢ/
“የግብ ጠባቂዎችን አቅም ለማሳደግ ስልጠና ሲዘጋጅ የሌሎች ክለቦችም ባለሙያዎች ይገኛሉ ለዚህ ነው መቻል ለኢትዮጵያ የምንለው”
የፊፋ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
/ የክለቡ ቴክኒካል ዳይሬክተር/
“ደጋፊውን የተነጠቀ.. የተረሳ …ላለመውረድ የሚጫወት ብር የሚያዋጣ ሰራዊቱ የሚወክለው ቡድን እንዳለ ያላወቀውን መቻልን ወደቀደመ ስሙ መመለስ የግድ ነው” ሲሉ ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ተናገሩ።
የመቻል 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ከ ሰኔ 1-30/2016 ድረስ “መቻል ለኢትዮጵያ ” በሚል መሪ ቃል በይፋ እንደሚከበር በመኮንኖች ክበብ ትላንት መግለጫ የተሰጠ ሲሆን የመቻል ስፖርት ክለብ የቦርድ አባል ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው እንደገለጹት ” በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ የመሆናችን የተሰራው ጠንካራ ሪፎርም ውጤት ማምጣት መጀመሩ ነው ከዚህ በፊት የነበሩት ቦርዶች የአቅማቸውን ሰርተዋል። እንደ ቦርድ ግን ቡድኑን ለማጠናከር ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ማለት አይቻልም ይሄ ቦርድ ግን ጠንካራ ስራ ሊሰራ ተዘጋጅቷል” ሲሉ ጄኔራሉ ተናግረዋል።
መቻል በዳኞች እየተበደለ ነው በሚለው ዙሪያ ጄኔራሉ በሰጡት አስተያየት ” የዳኝነት ስህተት መላው አለም ላይ ያለ የነበረ የሚኖር በመሆኑ እንደ ችግር አናየውም እንኳን እኛ ሀገር ቀርቶ በመላው አለምም ዳኛ እየተደገፈም ይሳሳታል በእ መነጋገሪያ ማድረግም አይገባም” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
መቻልን ከሰራዊቱ በላይ ህዝቡ ይደግፈዋል የሚለው እውነት ነው ሰራዊቱ ምን አውቆ ይደግፍ ይሄ ሆን ብሎ የታቀደ ነው ሰራዊቱን ከመቻል የመለየት ስራ ተሰርቷል።
80ኛ አመት ክብረ በዓላችንን የምናከብረው የተዛነፈውን ታሪካችን ለማደስና ለማስተካከል ነው እንደ እኛ መቻል የህዝብ ነው መቻልን መደገፍ ማጀገን ሰራዊቱን ማበርታት ነው ህዝቡ ከእኛ ጎን መሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል።
የቦርዱ ም/ል ሰብሳቢና የአዋሽ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ጸሃዬ ሽፈራው በበኩላቸው” መቻል ውስጥ ውጤት ለሜምጣት ጠንክረን እንሰራለን አስካሁንም ጥሩም እየሰራን ነው ቁርጠኛ አቀምም ይዘን እየሰራን ነው ነገር ግን የማያሰራ ነገር ካለ ግን ጥለን ነው የምንሄደው….. በመቻል የኢት ስፖርት ታሪክ እንቀይራለን ብዬ አምናለሁ ሰፊ ታሪክ ስኬታማ የሆነ ክለብ ነው ከሀገር አልፈን በአፍሪካ ምርጡን ክለብ እናሳያለን” ሲሉ ተናግረዋል ።
የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፉ ጌታሁንም እንደተናገሩት ለሌሎች ክለቦች ትምህርት የሚሆን አደረጃጀት ለመፍጠር እየሰራን ነው …ቦርዱ ቁርጠኛ አቋም አለው አመራሮች ስለ አደረጃጀትና ስለ ቀጣይ ዘመኑ በማሰብ ትልቅ ሀይል ፈጥረናል በዚህም ደስተኛ ነን… ትልልቅ ሰዎች ያሉበት ጠንካራ ስራ የሚሰራበት እንዴት መቻል ይደግ የኢትዮጵያ ስፖርት እንዴት ይቀየር የሚል እሳቤ ያላቸው መሪዎች በመኖራቸው ተደስቻለሁ የእግርኳስ ቡድኑን ምርጥ ቡድንና ኮከብ ተጨዋች የሚመጣበት ለማድረግ እየሰራን ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
የቡድኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር የፊፋ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ቡድኑን ጠንካራ ለማድረግ ጠንክረን እየሰራን ነው የ80ኛ አመት መታሰቢያ ክብረ በአል አንዱ አካል የሆነው ኢንተርናሽናል ውድድር አዘጋጅቷል። ሀምሌ 7/2016 የኡጋንዳው ኪታራ ከመቻል ጋር ባለሀብቶች ከባለስልጣናት አርቲስቶች ከመቻል የቀድሞ ተጨዋቾችና የብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጋር ይጫወታሉ” ብሏል።
ከባለሙያ ማብቃት ጋር ተያይዞ የካፍ ዲ ላይሰንስ በመቻል ጠያቂነት የሚሰጥ ሲሆን ከወንድ ቡድናችን 5.ከሴቶች ደግሞ .3 ሴቶች ስልጠና ይወስዳሉ ከሌሎች ክለቦች ባለሙያዎችም መጥተው እንዲወስዱ እናደርጋለን እንደ ሀገር ያለብንን የግብ ጠባቂዎች ችግር ለመቅረፍ የራሳችንን ግብ ጠባቂዎችን አቅም ለማሳደግ ስልጠና የሚዘጋጅ ሲሆን የሌሎች ክለቦችም ባለሙያዎች እንዲገኙ እናደርጋለን ለዚህ ነው መቻል ለኢትዮጵያ የምንለው ሲል ተናግሯል።
በ80ኛ አመት ክበረ በአል ላይ 35 ሺህ ሰው የሚሳተፍበት የሩጫ ውድድር የተዘጋጀ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ የሩጫውና የደጋፊው ማሊያ ሽያጭ መጀመሩ ታውቋል።