ዋልያዎቹ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ጥሪ አቀረቡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የማዳጋስካር አቻውን የፊታችን ረቡዕ ከቀኑ 10:00 ሰዓት በ ባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ያስተናግዳል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድናቸውን ለማጠናከር ተጨማሪ ሁለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው አካተዋል።

ይህንንም ተከትሎ የ ኢትዮጵያ ቡናው ወንድሜነህ ደረጀ እና የ ሰበታ ከተማው መሳይ ጳውሎስ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የተደረገላቸው አዳዲስ ተጫዋቾች መሆናቸውን የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor