አዲሱ የክለቦች የክፍያ ስርዓትን በተመለከተ በካፒታል ሆቴል ለስፖርት ጋዜጠኞች ማብራሪያና ነግንዛቤ ማስጨበጪያ እየተካሄደ ነው።
በዚህ መርሃግብር መክፈቻ ላይ ማብራሪያ የሰጡት
አቶ ክፍሌ እንደተናገሩት ” የክፍያ ችግርና የተጨዋቾች ክስ ሊጉ ከተጀመረ ጀምሮ ያልተፈታ ችግር ነው 3 ተጨዋቾች ሲያሟሙቁ የሚታይበት ሌሎቹ ተጨዋቾች ተለምነው የሚጫወቱበት ሊግ መሆኑ መስተካከል አለበት” ሲሉ ገልጸዋል።
” 75 በመቶ ክለቦች ለተጨዋቾቻቸው ወርሃዊ ክፍያ አይከፍሉም በጥናቱ መሰረት ይሄ ከቀጠለ ሊጉን የማቆም ስጋት በመፍጠሩ ይሄ የክፍያ ስርዓት ወጥቷል” ያሉት አቶ ክፍሌ ” 16ቱ ክለቦች እንዳይዋረዱ ጥናቱ የግድ መተግበር አለበት የተጨዋች ደመወዝ ሳይከፈል ጨዋታ ቢቋረጥ ለሊጉ ትልቅ ውርደት ይሆናል የወጣው መመሪያ ይህን የሚያስወግድ እንደሚሆን አምናለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
” በእግርኳሱ ሙስና አለ የገንዘብ ክፍተትም አለ ለሚለው ማህበረሰባችን ምላሽ የሚሰጥ መመሪያ ነው ” ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ “ጥናቱ መተግበሩን የሚቆጣጠረው አዲስ ኮሚቴ ተዋቅሯል። የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ አባል የሚሆኑበት ከጸረ ሙስና ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ከመረጃና ደህንነት ፣ ከሂሳብ ባለሙያዎችና ከህግ ክፍሉ የተካተተበት ጠንካራ ኮሚቴ ተዋቅሮ መመሪያው መተግበሩን በመከታተል ርምጃ ይወስዳል” ሲሉ ጥናቱ ተጀምሮ እንደሚቆሙት እንደሌሎቹ ጥናቶችና መመሪያዎች እንደማይሆን አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
- ማሰታውቂያ -
የተፈጠረውን አደጋ ለመከላከል 6 ወር የፈጀ ጥናት ተደርጎ 16ቱም ክለቦች ጥናቱ ዘገየ ሲሉ በመመሪያው ላይ ቅሬታ እንደሌላቸው መግለጻቸው ታውቋል።