የአዉሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን ከአጋር አካላት ጋር ከአርብ ጀምሮ ስለሚያደርጉት የእግርኳስ ዉድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል

ኢትዮ አዲስ የጤና ስፖርት ማህበር ፣ ከሻላ የጤና ስፖርት ማህበር ፣ ከአዉሮፓ ባህል እና ስፖርት ፌደሬሽን እንዲሁም ከሌሎች አቻ የጤና ማህበራት ጋር በመተባበር ለመከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ለማድረግ የፊታችን ጥር 6 7 እና 8 በአስር ቡድኖች መካከል የእግርኳስ ጨዋታ ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

ዉድድሩን አስመልከቶ ትላንት ከሰዓት መገናኛ አካባቢ በሚገኘዉ ቤልቪዉ ሆቴል በተሰጠዉ መግለጫ ስለ ዉድድሩ ሰፋ ያሉ አጠቃላይ ሀሳቦች የተነሱበት ሲሆን በመግለጫው ወቅት ከተነሱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም :-

ከሁለት አመት በፊት ዉድድሩን ወደ ኢትዮጵያ ለማዉጣት አስበን የነበረ ቢሆንም በኮሮና ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። አሁን ላይ በዋናነት ዉድድሩን ወደዚህ ለማምጣት ያቀድንበት ምክንያት ከሚገኘዉ ገቢ ለመከላከያ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ሲሆን ፤ ለዚህ ዉድድር መሳካት የተለያየ ድጋፍ ላደረጉልን አካላት ምስጋናችን የላቀ ነዉ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚን ዉድድሩን ለማካሄድ ስለፈቀዱልን ማመስገን እፈልጋለሁ ሲሉ በአዉሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አሳየ ጥላሁን ገልጸዋል።

ከሳቸው በመቀጠልም በአዉሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ዉድድር እና ስነስርዓት ኮሜቴ አባል የሆኑት አቶ መስፍን ታምራት በበኩላቸው :-

እንደሚታወቀው ይሄንን ዉድድር በሀገራችን ኢትዮጵያ ለማድግ ስንመጣ የመጀመሪያችን እንደመሆኑ መጠን ትልቁ እና ዋነኛው ነገር በሰላም እና ባማረ ሁኔታ ዉድድራችንን መጨረስ ነዉ። በቀጣይነትም ዉድድሩን በኢትዮጵያ ለማድረግ ይህ ጅማሯችን ማመር አለበት። ይሄንንም ለማሳካት ከተለያዩ የጤና ቡድኖች ጋር ጠንካራ ስራ ሰርተናል ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

ዉድድሩ አርብ በኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ የሚጀመር ሲሆን በዕለቱም የምድብ ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። በአስር ቡድኖች መካከል የሚደረገው ዉድድርም ዕለተ ቅዳሜ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተደርገዉበት እሁድ ፍፃሜዉን የሚያደርግ ይሆናል።

ዉድድሩን ለመታደም ሁሉም የስፖርት ቤተሰብ በስፍራው እንዲገኝ ያሳሰቡት አቶ ፋሲል የመግቢያ ዋጋውም 50 ብር መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ፍሬዉ ሀይለገብርኤል በስፍራው በዕንግድነት ተገኝቶ ዕጣ ያወጣ ሲሆን አሰልጣኙ ባወጣው ዕጣ መሰረትም ምድቡ የሚከተለውን ይመስላል።

ምድብ-1

° ኢሮፕ-1
° የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና የጤና ስፖርት ማህበር
° ኢትዮ አፍሪካ የጤና ስፖርት ማህበር
° አበበ ቢቂላ የጤና ስፖርት ማህበር
° አዳማ ጤና ለሰላም ስፖርት ማህበር

ምድብ-2

° ኢሮፕ-2
° የስታዲየም ዙሪያ የጤና ስፖርት ማህበር
° ኳስ ሜዳ የጤና ስፖርት ማህበር
° ኢትዮ አዲስ የጤና ስፖርት ማህበር
° ሻላ የጤና ስፖርት ማህበር

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *