የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ግንቦት 19 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ስድስት በመሸናነፍ ሁለቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 24 ጎሎች በ22 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 41 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሶስት ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።
በሳምንቱ በስድስት ተጫዋቾች ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል። ካርሎስ ዳምጠው(ድሬደዋ ከተማ)፣ አዳነ በላይነህ(ወልቂጤ ከተማ) እና ምኞት ደበበ(ፋሲል ከነማ) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ፤ ጋቶች ፓኖም(ፋሲል ከነማ) እና ፀጋአብ ዮሐንስ(ሃዋሳ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ለፈፀሙት ጥፋት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ እንዲሁም ሙና በቀለ(ሀምበሪቾ) በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ፋሲል ከነማ-ዋና አሰልጣኝ/ በውድድር አመቱ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ቢጫ ካርድ የተመለከተ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደንብ መሠረት አሰልጣኙ 1/አንድ ጨዋታ እንዲታገዱና ብር / 5000 /አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ ወስኗል።