የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከሁለት ቀናት በፊት በተደረጉ የማጠቃለያ ጨዋታዎች መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የኮከቦች የሽልማት እና የዕውቅና መርሐግብር በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል።
በመርሐግብሩም በተለያዩ ዘርፎች ኮከቦችን ይፋ የማድረግ እና ሽልማት የማበርከት መርሐግብር ተካሂዷል።
ኮከብ ተጫዋች – እንዳልካቸው መስፍን(አርባምንጭ ከተማ)
ኮከብ ግብ ጠባቂ – አሸብር ተስፋዬ(አርሲ ነገሌ)
ኮከብ አሰልጣኝ – ደስታ ደሙ (አርባምንጭ ከተማ)
ኮከብ ግብ አስቆጣሪ – አህመድ ሁሴን(አርባምንጭ ከተማ) እና ዳንኤል ዳርጌ(አርሲ ነገሌ)
ምስጉን ዋና ዳኛ – በሀይሉ ጌታቸው
ምስጉን ረዳት ዳኛ – ስንታየሁ ቶሎሳ
- ማሰታውቂያ -
በተጨማሪም የዓመቱ ምርጥ 11 ተጫዋቾች በ1-4-4-2 አሰላለፍ ይፋ ተደርገዋል።
ግብ ጠባቂ
አሸብር ተስፋዬ(አርሲ ነገሌ)
ተከላካዮች
ሳሙኤል አስፈሪ(አርባምንጭ ከተማ)
ነፃነት ገብረመድህን(ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
አበበ ጥላሁን(አርባምንጭ ከተማ)
ያሬድ የማነ(ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
አማካዮች
ኦካይ ጁል(ሀላባ ከተማ)
እንዳልካቸው መስፍን(አርባምንጭ ከተማ)
ሰለሞን ገመቹ(አርሲ ነገሌ)
ሰለሞን ጌታቸው(ነቀምቴ ከተማ)
አጥቂዎች
አህመድ ሁሴን(አርባምንጭ ከተማ)
ዳንኤል ዳርጌ(ኦሮሚያ ፖሊስ)
በመርሐግብሩ በኮከብነት የተሸለሙት ተጫዋቾች እያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር ተሸላሚ እንደሚሆኑም ተገልጿል።
በተጨማሪም በዕለቱ አዲሱ የከፍተኛ ሊጉ ሎጎ ይፋ ተደርጓል። ተያይዞም ከክለብ ላይሰንሲንግ ጋር በተያያዘ የተሻሉ ስራዎችን በመስራት ለሌሎች ክለቦች አርአያ ናቸው የተባሉት ደብረብርሃን ከተማ እና ቤንች ማጂ ቡና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
በተያያዘም በቀጣይም የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ፣ የወንዶች አንደኛ ሊግ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ተመሳሳይ የሽልማት እና የእውቅና መርሐግብር እንደሚካሄድ ተግልጿል።