ባለፉት ወራቶች በእስር ላይ የነነበሩት የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገ/መስቀል ከእስር ተለቀቁ።
አቶ አብነት በህመም ምክንያት ክሱ እንዲቋረጥ ያቀረቡትን ጥያቄ የተቀበለው የልደታ ምድብ 1ኛ ጸረ ሙስና ችሎት በክሱ ስማቸው የተካተተው የአምስቱንም ተከሳሾች ክስ ማቋረጡን አስታውቋል።
ይህን ተከትሎ አቶ አብነት ቅዱስ ጊዮርጊስ የገጠመውን አጠቃላይ የውስጥ ችግር ለማስወገድ ካሉት የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ከፍተኛ ስራ የሚጠበቅባቸው ይሆናል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የፕሬዝዳንቱን ከእስር መፈታት አስመልክቶ በቀጣይ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።