በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ27-30ኛ ሳምንት 32 ጨዋታዎችን በአዲስ አበባ ስታዲየም ለማካሄድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍቃድ እየተጠበቀ መሆኑ ተነገረ ።
ከፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በተገኘ መረጃ ውድድሩን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ለከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ደብዳቤ መላኩ ታውቋል። ባለፉት አመታት ሲሰራበት እንደነበረውና በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ ፣በባህርዳርና በአዳማ በተካሄደው የሊጉ መርሃግብር የየከተሞቹ አስተዳደር የጸጥታም ይሁን ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሀላፊነት በመውሰድ ውድድሩ ሲካሄድ መቆየቱ ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ስታዲየም ከ3 አመት በኋላ የሊጉን ውድድር ያስተናግዳል ተብሎ በከተማው እግርኳስ አፍቃሪያን በትልቅ ጉጉት እየተጠበቀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በኩል እውቅና ሰጥቶ ሃላፊነት ከወሰደ ከ27ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት ያሉት ጨዋታዎች በአዲስ አቧባ ስታዲየም ሊካሄድ ፍቃድ ካልተገኘ ግን ከ27-30ኛ ሳምንት ድረስ ያሉት 32 ጨዋታዎች በሀዋሳ የሚቀጥሉ መሆናቸው ታውቋል።
በዋሊያዎቹ ሁለት የማጣሪያ ጨዋታዎች የተቋረጠው የሊጉ መርሃግብር በቀጣዩ ሳምንት የሚቀጥል ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ56 የጥብና 26 ግብ እየመራ መሆኑ ይታወቃል።