የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ለሚያደርጋቸው የምድብ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎች የመጨረሻ የ23 ተጫዋቾች ስብስቡን አሳውቋል።
ቡድኑ አስቀድሞ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጎ የነበረ ሲሆን ያሬድ ባየህ ፣ ሔኖክ አዱኛ እና ቸርነት ጉግሳ በጉዳት ምክንያት አስቀድመው በስብስቡ ሳይካተቱ ቀርተዋል።
ጊት ጋትኩትን ወደ ስብስቡ አካቶ ዝግጅቱን ሲያደርግ የሰነበተው ቡድኑ ከነበሩት የ24 ተጫዋቾች መካከል የባህርዳር ከተማውን ሀብታሙ ታደሰን በመቀነስ 23 ተጫዋቾች በመያዝ ወደ ቢሳው ያመራል።
በዚህም በብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ 23 ስብሰብ በግብ ጠባቂነት ሰይድ ሀበታሙ ፣ ፍሬው ጌታሁን እና አቡበከር ኑራ በተከላካይነት ጊት ጋትኩት ፣ ብርሀኑ በቀለ ፣ ፍሬዘር ካሳ ፣ ሚልዮን ሰለሞን ፣ ፈቱዲን ጀማል ፣ ፍቅሩ አለማየሁ ፣ ረመዳን ዩሱፍ እና ያሬድ ካሳዬ ተካተዋል።
- ማሰታውቂያ -
በአማካይ ስፍራ ጋቶች ፓኖም ፣ ብሩክ ማርቆስ ፣ ወገኔ ገዛኸኝ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ ፣ ፉአድ ፈረጃ ፣ ቢንያም በላይ ፣ አብነት ደምሴ እና ቢንያን አይተን ሲካተቱ በአጥቂ ስፍራ ከነአን ማርክነህ ፣ ቢንያም ፍቅሩ ፣ መስፍን ታፈሰ እና ምንይሉ ወንድሙ ተካተዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ በነገው ዕለት ወደ ቢሳው የሚያመራ ሲሆን በመጪው ሐሙስ ከጊኒ ቢሳው አቻው ጋር ቢሳው ከተማ ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።