By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: “ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወሰዳቸው አብዛኛዎቹ ዋንጫዎች ውስጥ በተጨዋችነትም ይሁን በአሰልጣኝነት ስላለሁበት ኩራት ይሰማኛል” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ /ቅዱስ ጊዮርጊስ/
Share
Notification Show More
Latest News
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አካውንት ታገደ
አትሌቲክስ ዜናዎች
ሁለት ተጫዋቾች የአራት ጨዋታዎች ዕገዳ ሲጣልባቸው ሶስት ክለቦች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ከአራት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህርዳር ከተማ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅዳሜውን ጠቅላላ ጉባኤን አገደ….
አትሌቲክስ ዜናዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
ወላይታ ድቻ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ ድሬዳዋ ከተማ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ቃለመጠይቅቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወሰዳቸው አብዛኛዎቹ ዋንጫዎች ውስጥ በተጨዋችነትም ይሁን በአሰልጣኝነት ስላለሁበት ኩራት ይሰማኛል” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ /ቅዱስ ጊዮርጊስ/

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 5 months ago
Share
SHARE

ቅዱስ ጊዮርጊስ ፕሪሚየር ሊጉን በታሪክ ለ16ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋግጧል…. ባለፉት 24 አመታት ፈረሰኞቹን ያህል በሊጉ የነገሰ አንድም ክለብ አልተገኘም….ከ5 አመታትም የተዳከመ የሊግ ጉዞ በኋላ ባለፉት ሁለት አመታት ጊዮርጊሶች የለመዱትን ቦታ ዳግም ተቆናጠውታል…የዚህ የዙፋን መንበር ተረካቢና ተፋላሚ ደግሞ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ሆኗል በሊጉ ታሪክ ሁለትና ከዚያ በላይ በተከታታይ ያሸነፉ አሰልጣኞች አሰልጣኝ ዘሪሁንን ጨምሮ ስድሰት አሰልጣኞች ናቸው ከስድስቱ አምስቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኞች መሆናቸው ደግሞ ስኬታቸውን ትልቅ ያደርገዋል… የሀትሪክ ድረገጽ ባልደረባ የሆነው ዮሴፍ ከፈለኝ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን እንዲህ አነጋግሮታል…..

ሀትሪክ:-የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለሁለት ተከታታይ አመታት በማንሳት 6ኛው አሰልጣኝ መሆን ምን ስሜት ይፈጥራል…?

ዘሪሁን:-ካሰለጠኑኝ አብሬ ከሰራኋቸውም አሰልጣኞች እኩል ታሪክ ውስጥ መግባት ያስደስታል…ትልቅ ርካታ ፈጥሮልኛል ከነሱ እኩል እሆናለሁ ብዬ አላሰብኩም ግን በመሳካቱ በምወደው ክለብ ታሪክ ውስጥ በመገኘቴ ኮርቻለሁ ለተሻለ ነገር እንድጥር ትልቅ ሞራልና ደስታ አግኝቻለሁ።

- ማሰታውቂያ -

ሀትሪክ:-ከአምስቱ አሰልጣኞች ጋር ያለህ ትውውቅ እንዴት ይገለጻል..?

ዘሪሁን:-ሚቾ እኔ ተጨዋችነት ሳቆም ነው የመጣው ኮርስ እየሰጠኝ አካዳሚ እንድማር ያደረገኝ እሱ ነው… ብዙ ነገር እንዳገኝ አድርጎኛል.. ከወጣት ቡድን ጀምሮ አሰልጥኖ ትልቅ ደረጃ እንድደርስ ያደረገኝ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ነው አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ደግሞ አሳድጎ ያሰለጠነኝ አሰልጣኜ ነው አሰልጣኝ ገብረ መድህን ደግሞ ከህጻንነቴ እንዳደኩ ጁስም ምንም አምጥቶ ብዙ ድጋፍ አድርጎ ኮትኩቶ ትልቅ ደረጃ እንድደርስ ትልቁን ሚና ተወጥቷል እሱ መጫወት ሊያቆም እኔ ደግሞ ከወጣት ቡድን እያደኩ ነበረና በእድገቴ ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል ማርቲን ኖይ ደግሞ አብሬው ሆኜ በምክትልነት ዋንጫ አምጥቻለሁ ሁሉም በኔ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው በዚህም ትልቅ ኩራት ይሰማኛል

ሀትሪክ:-ከ2014 እና ከ2015 ትልቅ ትግል የገጠመህ ውድድር የትኛው ነው..?

ዘሪሁን:- የመጀመሪያም በመሆኑ ትልቅ ውጣውረዶች በመኖራቸው የ2014 ዋንጫ ይበልጥብኛል።ከፊትዋ በወቅቱ ያሉት አጥቂዎቼን ጨምሮ የተጨዋች ጉዳት አጥቅቶናል …የተሻለ ነገር ተጨዋቾቼም ከኋላ ወደ ፊትም እያመጣን እየጠጋገንም የተጫወትንበት ጊዜ ነበረና የአምናው ውድድር አስቸጋሪ ነበር..የ2015 ትግልም ግን ቀላል አይደለም..በሳይኮሎጂ አሳድገን ቴክኒካል ዲሲፕሊንድ አድርገን በጋራ የተሻለውን ቅዱስ ጊዮርጊስን ፈጥረን 16ኛውን የሊግ ዋንጫ ዘንድሮም በማንሳታችን ደስተኛ ነኝ።

ሀትሪክ:- በተጨዋችነት ስንት ዋንጫ አነሳህ..?

ዘሪሁን:- በተጫወትኩባቸው አመታትም ላይ በርካታ የሊግ ዋንጫ አንስቻለሁ ከ1985-1996 በነበረኝ የ12 አመት ቆይታ የጥሎ ማለፍ፣ የአሸናፊዎች አሸናፊ መሃል በብዙዎቹ የክለቡ ድል ውስጥ በመኖሬ ኩራት ይሰማኛል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተመሰረተ ጀምሮ ማንም ያላደረገውን ዋንጫ በማሸነፌ ደስተኛ ነኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወሰዳቸው አብዛኛዎቹ ዋንጫዎች ውስጥ በተጨዋችነትም ይሁን በአሰልጣኝነት ስላለሁበት ኩራት ይሰማኛል።

ሀትሪክ:- የተለየ የምትጠራቸው ተቀናቃኞቼ ነበሩ የምትላቸው ክለቦች አሉ..?

ዘሪሁን:- ሁሉም ተፋላሚዎች ነበሩ የገጠሙን በሙሉ ተቀናቃኝና ተፋላሚዎቻችን ነበሩ.. እውነት ለመናገር ለእኛ የአመቱ 30 ጨዋታዎች የዋንጫ ነበሩ የወረዱት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ለገጣፎ ለገዳዲና አርባ ምንጭ ሳይቀሩ ለእኛ ጠንካራ ተጋጣሚ ነበሩ ጠንካራ ፍልሚያ ስለሚጠብቀን ትልቅ ትኩረት ሰጥተን ነው እያንዳንዱን ጨዋታ ስንፋለም የነበረው .. ሁሉም ክለቦች መቶ ፐርሰንት ላይ ሆነው ሊፋለሙን ሲመጡ ተጨዋቾቻችን በተቃራኒው 200 ፐርሰንት እየሆኑ እየጠበቋቸው ጠንካራ አድርገውናል መናገር የምፈልገው አስራ አምስቱም ክለቦች ከእኛ ጋር ሲጫወቱ ይዘው የሚቀርቡት ጠንካራ አቋምን በሁሉም ጨዋታ ላይ ቢያደርጉት የሀገራችን እግርኳስ በተሻለ ያድጋልና ቢያስቡበት ብዬ አስባለሁ ከ30ው ፍልሚያ ሁለት ጨዋታ ተሸንፈን ነው ዋንጫ ያነሳነው ያ ደግሞ የነበረንን ጥንካሬ፣ ያደረግነውን ጥረት ያለንን ህብረት የሚያሳይ ይመስለኛል በዚሁ አጋጣሚ ለተጨዋቾቼ እንደምኮራባቸው መግለጽ እፈልጋለሁ

ሀትሪክ:- ዋንጫው ከእናንተ እንደማይወጣ የተሰማህ በየትኛው ጨዋታ ነው..?

ዘሪሁን:- ከባህርዳር ከተማ ጋር አቻ ወጥተን የነበረንን የ5 ነጥብ ልዩነት ማስጠበቃችንን ሳረጋግጥ ነው ዋንጫውን እንደምንወስድ ያመንኩት.. ጨዋታውን ማሸነፍ ነበረብን ግን አቻም ሲጠናቀቅ ልዩነቱ በመጠበቁ አልተከፋሁም በነገራችን ላይ ከፊታችን ላለ ጨዋታ ብቻ ትኩረት እየሰጠን መጓዛችን ነው ለድል ያበቃን…

ሀትሪክ:- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የምትለው ነገር አለ…?

ዘሪሁን:- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች 12ኛ ተጨዋቾቼ ናቸው ሁለት አመት ሙሉ አዲስ አበባ ላይ ውድድር አልነበረምና በየሄድንበት እየመጡ ደስታችን ደስታቸው ስቃያችን ስቃያቸው ሆኖ የትኛውም ቦታ ላይ በመገኘት ለተጨዋቾቹ ድጋፍ ሰጥተው በጋራ ያገኘነው ድል በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ሁለት ተከታታይ በአጠቃላይ ደግሞ 16ኛውን ዋንጫ ሲነሳ የነሱ ድርሻ ትልቅ ነውና ማመስገን እፈልጋለሁ።

ሀትሪክ:- ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የሊግ ውድድሩ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ መንግስት ማሳወቁን እንዴት አየኸው…?

ዘሪሁን:- በጣም ተደስቻለሁ… የከተማዋ አራት አምስት ክለቦች በተጋጣሚዎቻቸው ሜዳ ላይ ሲጫወቱ የባለሜዳነት ጥቅም አጥተው ቆይተዋል… ሜዳዎች በዝናብ ጨቅይተው ሲበላሹ የትራንስፖርት ችግር ሲከሰት መጉላላቱ ሁሉ አለና ውሳኔው ትልቅ ትርጉም አለው የከተማው ክለቦች በሜዳቸው የመጫወት እድል ማግኘት ያስደስታል.. ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መቻል፣ ኢትዮጵያ መድንና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣይ ይህን እድል በማግኘታቸው ያስደስታል። ለእኛም ሆነ ለደጋፊዎቻችን ትልቅ ደስታ ነው።

ሀትሪክ:- አምና ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ባህርዳር ከተማና ኢትዮጵያ መድን በጥንካሬ ሲቀናቀኗችሁ ነበር…የትኛው ነው ከባድ ጊዜ..?

ዘሪሁን:- የአምናው ነው… እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ ትግል ነበረው ፋሲልም ጥሩ ጊዜ ነበረው.. አምና እስከ መጨረሻ ጨዋታ ተፋልመናል ዘንድሮ ባህርዳር ከተማና ኢትዮጵያ መድን ከሌሎቹ በተሻለ ተቀናቃኞች ነበሩ ከአምናው አንጻር ካየነው ግን ብዙ ክለቦች ጠንከር ያሉት ዘንድሮ ነው ከ22 ኛ ሳምንት ጀምሮ ነው እየወረዱ የመጡት… በዚሁ አጋጣሚ ሁለቱንም ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው በመጨረሳቸው እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።

ሀትሪክ:- ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት አቻ መውጣት ወይም ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ አያስደስትም ይላሉ አልተጋነነም..?

ዘሪሁን:- አልተጋነነም እውነት ነው …ማሸነፍና ማሸነፍ ብቻ ነው የሚጠበቀው…አቻና ሽንፈት አይፈቀድም አይቻልም የሚገጥመን ጫናም ከባድ ነው ይህን ባህል ለማስቀጠል ትልቅ ጥረትና ትኩረት ይጠበቃል አስር ጨዋታ አቨንፈን አስራ አንደኛው ላይ አቻ ስንወጣ እንተቻለን ..ማሸነፍ አቻ መውጣትና መሸነፍ ያሉ ነገሮች ቢሆኑም ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ግን አይፈቀድም ተቀባይነት የለውም

ሀትሪክ :- በማሸነፍ ደረጃ ስኬታማ የነበራችሁት በየተኛው ሜዳ ነው..?

ዘሪሁን:- አዳማ፣ድሬዳዋና ባህርዳር ውጤታማና ስኬታማ ጊዜያችን ነበር….የመጀመሪያው ሀዋሳ ላይ ግን ጥሩ አልነበርንም ሜዳዎቹ የምንፈልገውን ያህል ሆኖ አላገኘንም ይደርቃል አንዳንዴ ደግሞ ዝናብ ሆኖ ሜዳው ይጨቀይና የምንፈልገውን ሜዳ ሳይሆን መቅረቱ ጎድቶናል። ሶስቱ ከተሞች ጋር ግን ውጤታማ ነበርን

ሀትሪክ:- ደመወዝ አለመከፈል በጊዜ አለመድረስ ተጨዋቾቹ ላይ የፈጠረው ችግር ነበር…?

ዘሪሁን:- አልረበሸንም.. ያልተከፈለ ደመወዝም አልነበረም..ምናልባት አምስት ወይም ስድስት ቀን መዘግየት እንጂ የቀረ ደመወዝ የለም.. ነገር ግን ተጨዋቾቼ የፋይናንስም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ተቋቋቁመው የተሻለውን ቅዱስ ጊዪርጊስ አሳይተው ዋንጫውን በመውሰዳችን በተጨዋቾቼ እኮራባቸዋለሁ አዕምሮን በአንድ አላማ ላይ ትኩረት አድርጎ መሄድ ውጤታማ ያደርጋልና ብዙ ነገር ሳያጓጓን ችግር ቢኖር እንኳን ተቋቋቁመን ይህን ውጤት ስላገኘን ተደስተናል

ሀትሪክ:- ምስጋናህ ለነማን ይድረስ…?

ዘሪሁን:- የቅድሚያ ምስጋና ለመድሃኒያለምና ለእናቱ ኪዳነምህረት ይሁንልኝ እንደ ሁሌው ክብር የማየው በእነሱ ነው ሁለቴ ያሸነፍኩት በነሱ ነው ክብር ምስጋና ለነሱ ይሁን ከዚያ በመቀጠል በየሄድንበት 12ኛ ተጨዋቾች ለሚሆኑት ደጋፊዎቻችን ትልቅ ምስጋና ይድረስልኝ…አምነውብኝ ሀላፊነቱን ለሰጡኝ የቦርድ አመራሮች ለጽ/ቤትና ካምፕ ሰራተኞች ለሁሉም ምስጋናዬን አቀርባለው…. ዋናውን ስራ ለሰሩልኝ ተጨዋቾቼ አብረውኝ ለለፉ ለረዳቶቼና ለሙሉ የአሰልጣኞች ስብስብ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ለባለቤቴ ሶስና ሃይሌ፣ ለነቢዩ ለዮሃና፣ ለዮስቲና ለቤተሰቦቼ ለእናት ወንድምና እህቶቼ እንኳንም ደስ አላችሁ ማለትና ማመስገን እፈልጋለሁ። ሁሌም አብሮኝ ላለ ለውድ ጓደኛዬ እንዳሻው ሞላ እንኳን ደስ አለህ እንደ ቅርበትህ ድሉም የአንተ ነው ሁሉንም አመሰግናለሁ…

ሀትሪክ:- የመጨረሻ ጥያዌ…. አሰልጣኝ ዘሪሁን ለ2016 በተከታታይ ሶስት አመት ዋንጫ በመውሰድ ሀትሪክ ይሰራል ብለን እንገምት..?

ዘሪሁን:- ይሄ ወደፊት የሚታይ ነገር ነው ከእግዚአብሄር ጋር የተሻለ ነገር ለመስራት እጥራለሁ አሁን ላይ ሆኜ የምናገረው ነገር ግን የለም..

You Might Also Like

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አካውንት ታገደ

ሁለት ተጫዋቾች የአራት ጨዋታዎች ዕገዳ ሲጣልባቸው ሶስት ክለቦች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል

የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ከአራት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅዳሜውን ጠቅላላ ጉባኤን አገደ….

የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article የጨዋታ ዘገባ | ከሁለት አመታት በኋላ አርባምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ከፍተኛ ሊጉ ተመልሷል !!
Next Article የጨዋታ ዘገባ | የጣና ሞገዶቹ አመቱን በድል አገባደዋል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

18ቱ ዳኞች ኮቪድ 19 የለባችሁም ተባሉ

ዮሴፍ ከፈለኝ By ዮሴፍ ከፈለኝ 3 years ago
የ2011 ኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቀጥታ ውጤት /LIVESCORE/ ይከታተሉ
የጨዋታ ዘገባ | አፄዎቹ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል !!
የጨዋታ ዘገባ | ሲዳማ ቡና የ3 ለ 0 ድል ተጎናፅፏል
የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 1ኛ ሳምንት ጨዋታ በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?