የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ
ቀን 10:00 ⏰
🇪🇹 ኢትዮጵያ ከ ዚምባብዌ 🇿🇼
🏟 ባህር ዳር ስታዲየም
በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ያከናወነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምንም እንኳን ጨዋታውን በሽንፈት ቢያጠናቅቅም ድንቅ እንቅስቃሴን መመልከታችን ይታወሳል። በዛሬዉ ዕለትም በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ዋልያዎቹ በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም ከዙምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።
በዛሬዉ ጨዋታም በዙምባብዌ ብሄራዊ ቡድን በኩል ከቋሚ ተሰላፊዎች 8 ተጫዋቾችን እንደማያገኙ ተሰምቷል ፤ (በጉዳት እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኩል ደግሞ ሁሉም ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታዉቋል።
በጉጉት የሚጠበቀው የሁለቱ ሀገራት ጨዋታም ደጋፊዎች እንደማይታደሙበት የታወቀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታውን ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ገብተው እንዲታደሙ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ለፊፋ ደብዳቤ ቢያስገባም ሀገራችን በኮቪድ በቀይ ዝርዝር ውስጥ መካተቷ ተቀባይነት እንዳያገኝ አድርጎታል። በዚህ መሰረትም ፈቃድ ካገኙ የሚዲያ አካላት ውጪ በዝግ እንደሚካሄድ ካፍ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።
ከጨዋታው አስቀድሞ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ “ተረጋግተን ጨዋታውን ለማሸነፍ እንጫወታለን ከጋና ጋር በነበረው ጨዋታ ቢያንስ አንድ ነጥብ ማግኘት ነበረብን፣ ዛሬ በኳስ ቁጥጥር በልጠን ጨዋታውን ለማሸነፍ እንገባለን” ሲል ሃሳባቸዉን ሰጥተዋል።
ጨዋታዉንም ፊፋ ሚዲያ የስርጭቱን ሙሉ ለሙሉ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ በብቸኝነት በ ” YOUTUBE ” ቻናል የሚያስተላልፍ ይሆናል። ይህንንም ተከትሎ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬት ጨዋታውን ማስተላለፍ እንደማይችል ተሰምቷል።
አስተያየት ይስጡ