By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ለሊጉ የዋንጫ ክብር እየተፋለሙ የሚገኙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል ጨዋታዎቻቸውን ሲያሸንፉ ፤ ወልቂጤ ከተማም በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠበትን የድል ውጤት አስመዝግቧል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችኢትዮጵያ ንግድ ባንክአዳማ ከተማሀምበሪቾ ድራሜወልቂጤ ከተማየጨዋታ ዘገባመቻልሻሸመኔ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ለሊጉ የዋንጫ ክብር እየተፋለሙ የሚገኙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል ጨዋታዎቻቸውን ሲያሸንፉ ፤ ወልቂጤ ከተማም በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠበትን የድል ውጤት አስመዝግቧል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በሀያ ዘጠነኛዉ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ዕለት ጨዋታ ቀዳሚ መርሐግብር የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ከተማን 2ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

በተመጣጣኝ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ንግድ ባንኮች በተደጋጋሚ ጥሩ ጥሩ የሚባሉ የግብ ዕድሎችን በመፍጠር ረገድ የተሻሉ የነበሩ ቢሆንም ነገር ግን ያገኟቸዉን ዕድሎች ወደ ግብነት በመቀየር ረገድ ግን ደካማ ሁነዉ ተስተውሏል።

በዚህ ሂደት በጀመረዉ ጨዋታ በተቃራኒው ሻሸመኔ ከተማዎች በተደራጀ መከላከል በጨዋታዉ የመጀመሪያው አጋማሽ ሲንቀሳቀሱ የተስተዋለ ቢሆንም ነገር ግን በ40ኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አግኝተዋል። በዚህም በተጠቀሰዉ ደቂቃ ባሲሩ ዑመር ያሻማትን ኳስ ሱለይማን ሀሚድ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡ አጋማሹን በመሪነት እንዲያጠናቅቅ አስችሏል።

በሁለተኛዉ አጋማሽ ባንኮች የበለጠ ተጠናክረዉ ወደ ሜዳ ሲመለሱ በተቃራኒው ሻሸመኔ ከተማዎች ደግሞ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተለየ ተዳክመዉ እና ተቀዛቅዘዉ ሲንቀሳቀሱ የተስተዋለ ሲሆን በሙከራ ረገድም በአንድ ሁለት አጋጣሚ ጥሩ ሙከራ ያደረጉት ባንኮች በ63ተኛዉ ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ግብ አግኝተዋል። በዚህም ከግራ መስመር በኩል የተሰጠዉን የቅጣት ምት ኳስ የመስመር አጥቂዉ አዲስ ግደይ በግሩም ብቃት ወደ ግብነት በመቀየር የክለቡን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነት ወደ ሁለት ለዜሮ ከፍ ማድረግ ችሏል።

- ማሰታውቂያ -

ከግቧ መቆጠር በኋላ የባንኩ የፊት መስመር ተጫዋች ኤፍሬም ታምራት ከወደ ግራ መስመር በኩል በመልሶ ማጥቃት ያገኘዉን ኳስ ተቆጣጥሮ ሳጥን ዉስጥ ደርሶ በቀጥታ ወደ ግብ መትቶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በግብ ዘቡ አቤል ማሞ አማካኝነት ኳሷ ተመልሳለች። ሁለቱ ጎሎች ከተቆጠሩ በኋላ ጨዋታዉ ተጋግሎ የቀጠለ ሲሆን በተለይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በተሻለ በርካታ የግብ ዕድሎችን ማግኘት ቢችሉም ነገር ግን በመጠቀሙ ረገድ ተዳክመዉ ተመልክተናቸዉ ጨዋታዉም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

( በተመሳሳይ ሰዓት በሀዋሳ አርቲፊሻል ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ሀምበሪቾ ዱራሜን በጋዲሳ መብራቴ ጎሎች ታግዞ 2ለ0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ በሊጉ መቆየታቸዉን ሲያረጋግጡ ፤ በተቃራኒው ሻሸመኔ ከተማ ደግሞ ባደገበት አመት ከሊጉ መዉደቁን አረጋግጧል )

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ መቻል አዳማ ከተማን 3ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

በፈጣን ሽግግር በጀመረዉ የአመሻሹ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ መቻሎች ገና ከጅምሩ አንስቶ የተሻለ ብልጫ ያስመለከቱን ሲሆን በአምስተኛዉ ደቂቃ ላይም መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በረከት ደስታ ተከላካዩ ጀሚል ያዕቆብን ተጭኖ በመቀማት ያገኘዉን ኳስ እየገፋ ሄዶ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ ተፈጥሯዊ ባልሆነዉ ዕግሩ ኳሷን ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን በጊዜ መሪ ማድረግ ችሏል።

ገና በጊዜ ከተቆጠረችዉ ግብ በኋላ ምላሽ ለመስጠት መጣር የጀመሩት አዳማ ከተማዎች ለግብ የቀረበ ዕድል ማግኘት ችለዉ ነበር ፤ በዚህም ከግራ መስመር በኩል አህመድ ረሽድ ገፍቶ ያቀበለዉን ኳስ አድናን ረሻድ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ አላማዋን ሳትጠብቅ ወደ ዉጭ ወጥታለች።

ጥሩ ብልጫ የነበራቸዉ መቻሎች በ20ኛዉ ደቂቃ ላይ አዳማዎች በሰሩት ስህተት የተገኘዉን ኳስ ወደ ግብነት መቀየር ችለዋል ፤ በዚህም በተጠቀሰዉ ደቂቃ ከወደ ግራ በኩል ኳሷን እየገፋ ሳጥን ዉስጥ የገባዉ ሽመልስ በቀለ ለአጥቂዉ ምንይሉ ያቀበለዉን ኳስ ደርሶ ለማቋረጥ የሞከረዉ አህመድ ረሽድ ራሱ መረብ ላይ አሳርፏታል።

ጫናቸዉን ይበልጥኑ አጠናክረዉ የቀጠሉት መቻሎች በተጨማሪም በአማካዩ በሀይሉ አማካኝነት ከሳጥን ዉጭ ከርቀት የሚገርም ሙከራ ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሷ ለጥቂት በግቡ አግዳሚ አናት ላይ ወደ ዉጭ ወጥታለች።

በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ  ወደ ሜዳ ያስገቡት አዳማ ከተማዎች ያሰቡትን ያክል ጫና መፍጠር ባይችሉም በአድናይ ረሻድ ፣ ቦና አሊ እና ቢኒያም አይተን አማካኝነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ ነበር ፤ በ77ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን በጨዋታዉ ድንቅ የነበሩት መቻሎች በአማካዩ ሽመልስ በቀለ ግሩም ብቃት ታግዘዉ ሶስተኛ ግብ አስቆጥረዉ ጨዋታዉ 3ለ0 በሆነ ዉጤት በመቻል አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ፋሲል ከነማ ከወላይታ ዲቻ አቻ ሲለያዩ ፤ በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡናም መርሐግብራቸዉን በአቻ ዉጤት ደምድመዋል !!
Next Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ዘጠነኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንዜናዎችቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

3ቱም የትግራይ ክልል የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በ2014 የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አሳወቁ።

hatricksport team By hatricksport team 5 years ago
ሀብታሙ ወልዴ አዳማ ከተማን ተቀላቅሏል
ኢንስትራክተር ሠውነት ቢሻዉ ወደ ጋቦን ተጓዙ
​ሪፖርት | ሽረ እንዳስላሴ በሜዳው ከለገጣፎ ከተማ ጋር ነጥብ ተጋርቷል፡፡
“በትልቅ አሰልጣኝ ስር ለመስራት በመቻሌ እድለኝነት ይሰማኛል” ዱላ ሙላቱ /ሀዲያ ሆሳዕና/
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?