የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኔ 24 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 14 ጎሎች ተቆጥረዋል። 25 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።
በሳምንቱ በአራት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ሀቢብ መሀመድ(ፋሲል ከነማ) ፣ ዓለምብርሀን ይግዛው(ፋሲል ከነማ) ፣ ሰለሞን ወዴሳ(ሃዋሳ ከተማ) እና መክብብ ደገፉ(ሲዳማ ቡና) በአምስት ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።