የጨዋታ ዘገባ | ኢትዮጵያ ቡና የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ድል ተቀዳጅቷል

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባጅፋር ያደረጉት ጨዋታ ከግብ ርቆ በነበረው አቡበከር ናስር ሁለት ግቦች ታግዘው ቡናማዎቹ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ።

ከአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ቡናማዎቹ አራት ቅያሪ ሲያደርጉ ቴዎድሮስ በቀለ ፤ ያብቃል ፈረጃ ፤ ሀይሌ ገብረትንሳይ እና ሮቤል ተክለሚካኤልን እንዲሁም በጅማ አባጅፋር በኩል ደግሞ ስድስት ያህል ቅያሪ በማድረግ አድናን ረሺድ ፤ ምስጋናው መላኩ ፤ ሱራፌል አወል ፤ ታምራት ዳኜ ፤ ወንደወሰን ማርቆስ እና ተስፋዬ መላኩ ወደ ሜዳ መልሰው ጨዋታቸውን ጀምረዋል ።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ቡናማዎቹ ከኋላ በመጀመር በተለመደው አጨዋወታቸው ጨዋታውን ያደረጉ ሲሆን የሊጉ ግርጌ ላይ የተቀመጡት ጅማ አባ ጅፋሮች በመልሶ ማጥቃት እና አልፎ አልፍ በኢትዮጵያ ቡና ተጨዋቾች የሚሰሩ ስህተቶችን በመጠቀም የግብ ዕድል ለመፍጠር ሞክረዋል ።

16ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያውን ሙከራ ማድረግ የቻሉት ጅማ አባጅፋሮች በቀላሉ በአቤል ማሞ ተይዞባቸዋል ። የግብ ሙከራ በማድረጉ ረገድ የተሳናቸው ኢትዮጵያ ቡናዎች 43ኛ ደቂቃ ላይ ከቅጣት ምት በሀይሌ ገበር ትንሳይ አማካኝነት ያደረጉት ሙከራ በግቡ አግዳሚ ተመልሶ ወቷል ።

በሁለተኛው አጋማሽ ግብ ለማስቆጠር ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ቡናማዎቹ ብልጫ የታየበትትን አጋማሽ አስመልክቶን አልፏል ።

በ52ኛ ደቂቃ ላይ ከግብ ርቆ የነበረው አቡበከር ናስር ከየአብቃል ፈረጃ የደረሰውን ኳስ ተጠቅሞ የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ግብ በማስቆጠር ኢትዮጵያ ቡናን መሪ አደረገ ። ግቡ ከተቆጠረ ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ አቡበከር ናስር በድጋሚ ከሀይሌ ገብረትንሣይ የደረሰውን ኳስ ወደ ተጠቅም የቡናማዎቹን መሪነት ወደ 2 ለ 0 አሳደገ ።

ከግቦቹ መቆጠር በኋላ ጅማ አባጅፋሮች ተጭነው ለመጫወት የሞከሩ ሲሆን ጥሩ የሚባሉ የግብ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ኢላማዎቸውን ባለመጠበቅ እና በግብ ጠባቂው አቤል ማሞ ተመልሶባቸዋል ።

81ኛ ደቂቃ ላይ ጅማ አባጅፋሮች በዳዊት ፍቃዱ አማካኝነት ከሽንፈት ያልታደጋቸውን ግብ አስቆጠሩ ። ጨዋታውም በዚሁ ውጤት ተጠናቀቅ ።

ውጤቱን ተከትሎም ቡናማዎቹ ነጥባቸውን ወደ 5 ሲያሳድጉ እስካሁን ምንም ማሸነፍ ያልቻሉት ጅማ አባጅፋሮች ያለምንም ነጥብ የሊጉን ግርጌ ይዘዋል ።

Writer at Hatricksport

Facebook

Habtamu Mitku

Writer at Hatricksport