ኢትዮጵያ ቡና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ ጨዋታዉን ዛሬ ያደርጋል !!

ኢትዮጵያ ቡና በ2013 የዉድድር አመት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በሁለተኝነት ደረጃ ማጠናቀቁን ተከትሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ተሳታፊ መሆኑ ይታወቃል።

የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን ለወራት ያክል በቢሾፍቱ ሲከዉኑ የቆዩት ቡናማዎቹ በአዲስ አመት ዋዜማ አርብ ምሽት የመጀመሪያ ጨዋታቸዉን ለማድረግ ወደ ዩጋንዳ አምርተዋል።

አርብ ሌሊት ዩጋንዳ የደረሱት ኢትዮጵያ ቡናዎች በትላንትናው ዕለት የመጀመሪያ ልምምዳቸዉን ጨዋታዉ በሚደረግበት በሴንት ሜሪ ስታዲየም ሰርተዋል።

በዛሬዉ ዕለትም የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸዉን ከዩጋንዳው Ura ስፖርት ክለብ ጋር ከቀኑ 10:00 ላይ በዩጋንዳ ሴንት ሜሪ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።

የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ ታንዛኒያዉያን ዳኞች የሚመሩት ሲሆን ኮሚሽነሩ ደግሞ ከሩዋንዳ መሆናቸው ታዉቋል። በተጨማሪም የሁለቱ ክለቦች ጨዋታውበሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ SanyukaTv እንደሚተላለፍ ተጠቁሟል።

Writer at Hatricksport

Facebook

Ermias Misganaw

Writer at Hatricksport

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *