.. አጠቃላይ የአንድ አመት የዝግጅት ጉዞን በተመለከተ
ሃሙስ መግለጫ ሊሰጥ ነው…..
“በእናንተ ውስጥ እኛም አለን” በሚል መሪ ቃል በተለይ ሶስቱን የትግራይ ክለቦችን በገቢ ለመደገፍ እየተካሄደ ያለው ሁሉን አቀፍ ዘመቻን የሚያብራራ ጋዜጣዊ መግለጫ የፊታችን ሃሙስ በሸራተን አዲስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።
ስፖርት ለሰላም ስፖርት ለፍቅር ስፖርት ለሀገር አንድነት በተሰኘው በዚህ መርሃግብር ከጦርነቱ ማግስት ከፍተኛ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸውን ሶስቱ ክለቦች መቀለ 70 እንደርታ ፣ ወልዋሎ አዲግራትና ስሁል ሽረ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለሱ ለማድረግ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጭምር ጥሪ ያደረጉበት ብሄራዊ ቴሌቶን የአንድ አመት ጉዞን የመጨረሻን ምዕራፍ የሚያብራራ እንዲሁም ፕሮግራሙ መቼና የት እንደሚካሄድ የሚገልጽ ጋዜጣዊ መግለጫ ከነገ በስቲያ ሃሙስ ግንቦት 29/2016 በሸራተን አዲስ እንደሚሰጥ የትግራይ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በአቶ ተክላይ ፍቃዱ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ ያስረዳል።
ከፍተኛ የክልሉና የስፖርቱ አመራሮች የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሚገኙቨት የሸራተን አዲሱ መግለጫ ላይ መገናኛ ብዙሃኑ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።