መነሻ ገጽ መከላከያ መከላከያ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በኃላፊነት ሾሟል
መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

መከላከያ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በኃላፊነት ሾሟል

አጋራ
አጋራ

ከተከፈተ 8ኛ ቀኑን በያዘው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ራሱን እያጠናከረ ያለው መከላከያ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ለመቅጠር ተስማማ።

ከአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ውሉን እንደማያድስ ያስታወቀው መከላከያ ምክትሉ ዮርዳኖስ ዐባይን ጨምሮ ካሰናበተ በኋላ የተጨዋቾችን ዝውውር በመጪው አሰልጣኝ ጥቆማ ሲመርጥ መቆየቱ ታውቋል።

ከነዓን ማርክነህን ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በረከት ደስታን ከፋሲል ከነማ፣ ምንይሉ ወንድሙን ከወላይታ ድቻ በማስፈረም ራሱን ያጠናከረው መከላከያ ዛሬ ጠዋት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን አዲሱ አሰልጣኝ በማድረግ ለአንድ አመት አስፈርሞታል።

ባህርዳር ከተማና አዳማ ከተማን በዋና አሰልጣኝነት የሰራው አሰልጣኝ ፋሲል በቀጣይ ሁለት አመታት የአብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ሁለተኛ ክለብ ከሆኑት ተወዳጅ ጥቂት ክለቦች መሀል አንዱ የሆነውን መከላከያን ወደ ውጤት ማማ እንዲያወጣ ተስፋ ተጥሎበታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...