አጋራ

የ2014 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በሁለተኝንት ያጠናቀቁት ፋሲል ከነማዎች የነባር ተጫዎቻቸውን ውል በማደስ ላይ ተጠምደው የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ መናፍ ዐወልን ቀዳሚ ፈራሚያቸው በማድረግ አስተዋውቀዋል ።

መናፍ ዐወል በተጠናቀቀው የውድድር የባህርዳር ከተማን የኋላ መሰመር በአስተማማኝ ሁኔታ ሲመራ የነበረ ሲሆን ከባህርዳር ቀደም ብሎም በአዳማ ከተማ ተጫውቶ ማሳለፍ ችሏል ።

ከክለብ ቆይታዎች ባለፈም ከ23 አመት በታች እና በዋናው ብሄራዊ ቡድን ማልያ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል ።

ተጫዋቹ መቀመጫውን በጎንደር ከተማ ባደረገው ክለብ ለሁለት ዓመታት ለመቆየት የሚያስችለውን ፊርማ ያኖረ ሲሆን ወሳኙን ተከላካያቸውን ያሬድ ባየህን ያጡት ፋሲል ከነማዎች ጥሩ ምትክ ያገኙ ይመስላል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ኢትዮጵያ መድህንኢትዮጵያ ንግድ ባንክዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3-1 በማሸነፍ የአምስተኛውን ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በድል አጠናቀቀ!

በአቤኔዘር አበበ ኢትዮጵያ መድን በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቀ! በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ...