በኮስታሪካ እና ፓናማ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከቡሩንዲ ጋር ያከናወኑት የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴት ብሔራዊ ቡድን 5-0 በሆነ በሰፊ የጎል ልዩነት ረቷል።
ዛሬ ከቀኑ 10:00 ቡጁምቡራ አንዋሪ ስታዲዮም የተደረገው ይህ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ ብቻ አራት ግቦችን የኢትዮጵያ ሴቶች ቤሕራዊ ቡድን አስቆጥረዋል። ምርቃት ፈለቀም 6ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ግብ በማስቆጠር ሀገሯን ቀዳሚ አድርጋለች። ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ አማካኟ አረጋሽ ካልሳ ግብ ብታስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ ተብሎባታል። ብልጫን ወስደው መጫወት የቻሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚገኙት እድሎች ለመጠቀም ምንም አይናፋርነት አይሰተዋለባቸውም ነበር። 10ኛው ደቂቃ ታሪኳ ዴቢሶ ከማእዘን የተሻገረላትን ኳስ በጭንቅላቷ በመግጨት ያስቆጠረችው ግብ ማሳያ ነበር። በዛሬው ጨዋታ ጥሩ ስትንቀሳቀስ የነበረችው አማካኟ አረጋሽ ካልሳ በግምት ከ30 ሜትር ርቀት አክርራ የመታችው ኳስ አግዳሚው ለትሞ እጅግ ማራኪ ግብ በማስቆጠር ልዩነቱን ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ችላለች። ቤህራዊ ቡድናችን ጫና ፈጥሮ በመጫወቱ ምክንያት የቡሩንዲ ለተከላካዮች ስህተት እንዲፈፅሙ አስተዋፅኦ ከማድረጉም በላይ የሚያገኟቸውን አጋጣሚዎችንም ለመጠቀም ኮስታራ እርምጃን ወስደዋል። ለዚህም ማሳያ ሚሆነው 37ኛው ደቂቃ ላይ አጥቂዋ ረድኤት አስረሳህኝ የመታችውን ኳስ ወደ ውጭ አወጣለሁ ስትል የቡሩንዲዋ ተከላካይ በራሷ ግብ ላይ አስቆጥራለች። በዚህም ውጤት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጨማሪ ግቦች ሳይሰተናገድበት በኢትዮጵያ 4-0 በሆነ መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
የሁለተኛው አጋማሽ በሁለቱም በኩል ተመጣጣኝ ጨዋታ ቢኖርም የኢትዮጵያ ቤሕራዊ ቡድን ግን ግብ ለማስቆጠር ወደሗላ አላለም። 81ኛ ደቂቃ አጥቂዋ ረድኤት አስረሳህኝ የማሳረጊያዋን ግብ በማስቆጠር ሀገሯን 5-0 እንድታሸንፍ አስችሏታል። የመልስ ጨዋታውም ከሳምንታት በኋላ አዲስ አበባ ስታዲዮም ይደረጋል።
አስተያየት ይስጡ