መነሻ ገጽ Uncategorized ሪፖርት | በሊጉ  ፋሲልና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተው ደረጃቸውን ወደ መሪዎች በማስጠጋት የቻሉበትን ውጤት አስመዝግበዋል
Uncategorized

ሪፖርት | በሊጉ  ፋሲልና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተው ደረጃቸውን ወደ መሪዎች በማስጠጋት የቻሉበትን ውጤት አስመዝግበዋል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የ22ኛ ሳምንት የመርሀ ግብሩ የመጀመሪያ ብቸኛው ጨዋታ ዛሬ ጎንደር አጤ ፋሲለደስ ስታዲየም በተካሔደዉ 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማና አዳማ ከተማ ያለ ግብ 0 ለ 0 በሆነ ዉጤት ተለያዩ። ሁለቱ ቡድኖች ሰኞ ላለባቸዉ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ የጨዋታዉ ቀን ከእሁድ ወደ ዛሬ በተቀየረዉ ይህ ጨዋታ ባለሜዳዎች ባለፈዉ በወላይታ ዲቻ 3ለ0 ከተሸነፈዉ ቡድን ሶስት ያህል ተጫዋቾችን የቀየሩ ሲሆን የመሃል አማካዮችን ኤፍሬም አለሙና ኤርምያስ ሃይሉ በሙለቀን አቡሃይና በመጣባቸዉ ሙሉ ሲተኩ አጥቂዉ ፊሊፕ ዳዉዝን ደግሞ በራምኬሎክ ቀይረዉ አስገብተዋል።
የስራ ቀን መሆኑን ተከትሎ ከወትሮዉ በተለየ መልኩ የደጋፈዎች ቁጥር ቀዝቀዝ ብሎ በታየበት በዚህ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች የጨዋታዉ መጀመሪያ ፊሽካ ከተነፍበት ደቂቃ ጀምሮ በፍጥነት ወደ ጎል በመድረስና በሁለቱም በኩለ ጫና ፈጥሮ በመጫዎት ጀምረዋል። እንግዳዉ ቡድን አዳማዎች የጨዋታዉን የመጀመሪያ ሙከራ ለማድረግ ሁለት ደቂቃዎች ብቻ የፈጀባቸዉ ሲሆኑ ያገኙትን የማዕዘን ምት በረከት ደስታ ሲያሻማ የኳሷ አቅጣጫ ተቀይራ ጎል ከመሆን የዳነችዉ በፋሲሉ ግብጠባቂ ሚካኤል ሳማኪ ጥረት ነበር። ብዙም ሳይቆይ አዳማዎች በተመሳሳይ ያገኙትን የማዕዘን ምት ተሻምተዉ በዕለቱ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የዋለዉ የአዳማዉ ከነዓን ማርክነህ በግንባሩ ገጭቶ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ልትወጣበት ችላለች። ከዚህም ሌላ በረከት ደስታ በድጋሚ ከመሐል ሜዳ እየገፋ መጥቶ አክርሮ መትቶ ወደዉጭ የወጣችዉ በአዳማዎች በኩል ሊጠቀሱ የሚችሉ ሙከራዎች ነዉ። ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ጨዋታዉ ሪትም መግባት የቻሉት ፋሲሎች በጨዋታዉ 15ና 20 ደቂቃ በሐሚዝ ኪዛና በተከላካዩ ሰኢድ ሐሰን አማካኝነት ለጎል የቀረቡ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል። በሌላ በኩል ዛሬ በመስመር አጥቂነት የተሰለፈዉ ዪጋንዳዊው ያሳር ሙገርዋ ወደ ጎል ያሻማዉን ኳስ የአዳማዉ ግብ ጠባቂ ሲተፋዉ ሁለት የፋሲል ተጫዋቾች ባለመናበባቸዉ ምክንያት ያመከኗት ኳስ በአጤዎቹ በኩል የምታስቆጭ ሙከራ ናት። ሁለቱ ቡድኖች በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ ቢችሉም ኢላማቸዉን የጠበቁ ሙከራዎቸ ሳያደርጉ ጨዋታዉ ወደ እረፍት አምርቷል።

አጤዎቹ ሁለተኛዉን አጋማሽ ራምኬሎክን ወደ መስመር አዉጥተዉ ሐሚስ ኪዛን በፊት አጥቂነት በመቀየር የጀመሩ ሲሆን። ሁለተኛዉ አጋማሽ ከመጀመሪያው አንፃር እጅግ የተቀዛቀዘ ጨዋታ ሲሆን አልፎ አልፎ ብልጭ ከሚሉ የጎል እድሎች በስተቀር ይህ ነዉ ተብሎ ሊጠቀሱ የሚችሉ የጎል እድሎችን አልፈጠሩም። በ65ኛዉ ደቂቃ አዲስ ህንፃ ወደ ግብ አክርሮ መትቶ በጎሉ አግዳሚያ ላይ የወጣችዉና የአዳማ ተጫዋቾች በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ኳስ አንዳርጋቸዉ ይላቅ መትቶ ሳማኪ በቀላሉ ያዳነበት በአዳማዎች በኩል ሲጠቀሱ በባለሜዳዎች በኩል ደግሞ ራምኬሎክ በሁለት አጋጣሚዎች ወደ ግብ ሞክሮ ጃፍር ደሊል በአስደናቂ ብቃት ያዳናቸዉ ኳሶች ይጠቀሳሉ።
በጨዋታዉ 70ኛ ደቂቃ ላይ የአፄዎቹ የመስመር አጥቂ ራምኬል ሎክ ከመሐል የተሻገረለትን ኳስ ወደ ጎል ቢቀይረዉም የመስመር ዳኛዉ ከጨዋታ ዉጭ ነዉ በማለት ሽሮታል ይህንንም ተከትሎ የፋሲል ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ተቃዉሟቸዉን ሲገልጡ ተስተዉለዋል።

ብዙም ሳቢና ማራኪ ያልነበረዉ ሁለተኛ ሁለቱ ቡድኖች መሐል ላይ ያማከለ ጨዋታን ሲተገብሩ ተስተዉለዋል። በዚህም ጨዋታዉ ምንም ጎል ሳይቆጠርበት በአቻ ዉጤት ተጠናቋል።በዚህ ዉጤት መሰረት ሁለቱ ቡድኖች ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል በእኩል 33 ነጥቦች 4ኛና 5ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...