ሉሲዎቹ ከታንዛኒያ ጋር ያለግብ አቻ ተለያዩ

 

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎቹ ዛሬ ከታንዛኒያ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0-0 በሆነ ውጤት ሊያጠናቅቁ ችለዋል፤ በኡጋንዳ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተደረገ ባለው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሴካፋ ሻምፒዮና ላይ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ ረቡዕ ዕለት 10 ሰአት ላይ  ከሩዋንዳ ጋር ያደረጉት ሉሲዎቹ ጨዋታቸውን 3ለ2 በሆነ ውጤት ያሸነፉ ሲሆን በእለቱም ፍልሚያቸው የድሉን ግቦች በሉዛ አበራ የ3ኛውና የ64ኛው ደቂቃ  እንደዚሁም ደግሞ በመስከረም ካንኮ የ72ኛው ደቂቃ ግቦች ነው ለማሸነፍ የቻሉት፡፡ የታንዛኒያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድንም በፍልሚያው በመጀመሪያ ግጥሚያቸው ሩዋንዳን 3-2 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት ያሸነፉ በመሆኑ ሁለቱ ሀገራት ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ እኩል 4 ነጥብ እና 1 ግብ በመያዛቸው የምድቡ መሪን ለመለየት በወጣው ዕጣ ታንዛኒያ አንደኛ መሆኗ ግጥሚያውን በኤፍ ኤም 96.3  የዕጣ ማውጣቱ ላይ ሎዛ አበራ እና ሌሎች ተጨዋቾቹ አወጣጡ ተገቢ አይደለም በሚል ተቋውሞ እንዳሰሙም እየተነገረ ይገኛል፤ የእጣ ማውጣቱ ትክክል እና ተገቢ ከሆነ ሉሲዎቹ በግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ኬንያን የሚገጥሙ ይሆናል፤፤ ታንዛኒያ ደግሞ አዘጋጇን ትገጥማለች፡፡

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook