መነሻ ገጽ Uncategorized ​ለአትሌት ምሩፅ ይፍጠር በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የጸሎት ስነ ስርአት ተከናወነ 
Uncategorized

​ለአትሌት ምሩፅ ይፍጠር በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የጸሎት ስነ ስርአት ተከናወነ 

አጋራ
አጋራ

በካናዳ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በ72 ዓመቱ ከዚህ አለም በሞት ለተለየው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በቶሮንቶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የፀሎት ስነ ስርአት ተከናወነ።

በካናዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ቤተሰቦቹ እና በርካታ ኢትዮጵያውያን በፀሎት ስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል።


የሲ ቢ ሲ ዘገባ እንደሚያሳየው የአትሌት ምሩፅ ይፍጠር አስከሬን በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ይሆናል።

አትሌት ምሩፅ በ1972 ዓ.ም በሞስኮ በተካሄደው ኦሎምፒክበ10 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ተወዳድሮ ድርብ ወርቅ ለሀገሩማምጣት የቻለ ታሪካዊ አትሌት ነው።

ምሩፅ በ1964 ዓመተ ምህረትም በሙኒክ ኦሎምፒክ በ10 ሺህሜትር ለሀገሩ የነሐስ ሜዳሊያ ማስገኘት ችሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅና ነሀስ ሜዳሊያዎችን ለሀገሩ አበርክቷል።

በውድድር ፍጻሜ ላይ በተደጋጋሚ ሳይታሰብ ተፎካካሪዎችን አስከትሎ በሚገባበት አጨራረሱ “ማርሽ ቀያሪው” የሚል መጠሪያ ያገኘው ምሩፅ፥ ባለፉት ጥቂት ወራት በህመም ሲሰቃይ ቆይቷል።

ለህክምና ወጪውም ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከሙያ አጋሮቹ እና ከወዳጆቹ ድጋፍ ተደርጎለታል።

ይሁንና ያጋጠመው የጤና ችግር ፀንቶበት በካናዳ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ታህሳስ 14 2009 ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...