መነሻ ገጽ Uncategorized ​ለሁለት ክለቦች ፈርሞ የነበረው አክሊሉ አየነው የኢትዮጵያ ቡና ህጋዊ ተጨዋች ሆነ
Uncategorizedኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፋሲል ከተማ

​ለሁለት ክለቦች ፈርሞ የነበረው አክሊሉ አየነው የኢትዮጵያ ቡና ህጋዊ ተጨዋች ሆነ

አጋራ
አጋራ

የደደቢት ክለብ ጋር ከተለያየ በኃላ በኢትዮጵያ የክረምቱ ወራት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ለሁለት ክለቦች ማለትም ለኢትዮጵያ ቡናና ለፋሲል ከተማ ፊርማውን አኑሮ የነበረው  የተከላካዩ ስፍራ ተጨዋች አክሊሉ አየነው በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ጉዳዩ ለወራቶች ከታየለት በኃላ በመጨረሻም እልባት አግኝቶ ተጨዋቹ ለኢትዮጵያ ቡና እንዲጫወት ተወስኖለታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የክረምቱ ወራት የዝውውር መስኮት ላይ ለፋሲል ከተማ በሆቴል ውስጥ እንደዚሁም ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና  ሶስቱም ተዋዋይ አካላቶች በተገኙበት በእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት ውስጥ ፊርማውን አኑሮ የነበረው አክሊሉ በጷጉሜ 3 2009 ዓ.ም ለሁለት ክለብ መፈረሙን ተንተርሶ የዲሲፕሊን ኮሚቴው የ600 ሺ ብር  ቅጣት ጥሎበት የነበረ ሲሆን ተጨዋቹ  ለተጣለበት ቅጣት ተገቢ አይደለም በሚል ይግባኝ በመጠየቁና ለፋሲል  ከተማ የፈረመበት ሂደትም ከመተዳደሪያው መመሪያ ውጪ በመሆኑና ወደ ክርክር ውስጥ የሚያስገባውም ባለመሆኑ የፋሲል ከተማ ክለብም  ተጨዋቹን ያስፈረሙበት ሁኔታ 20 ሺ ከፍለው ህጋዊ ማድረግ ሲገባቸው ውሉን ሊጨርሱ ስላልቻሉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ በመጨረሻም ለአክሊሉ  ሁለት ቦታ መፈረም አግባብ እንዳልሆነ በተግሳፅ ከመከረው በኀላ ተጨዋቹ ለቡና እንዲጫወት ሊወሰን ችሏል፡፡
የደብዳቤው ሙሉ ይዘትም ይህን ይመስላል


አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...