ሀድያ ሆሳእና ፀጋይ ኪዳነማርያምን በዋና አሰልጣኝነት ቀጠሩ

 

በዚህ ሳምንት አሰልጣኝ ግርማ ታደሰና ረዳቶቹን ከስታቸው በማገድ ያሰናበተው ሀድያ ሆሳእና አንጋፋውን አሰልጣኝ ፀጋይ ኪዳነማርያምን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሯል።

በውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ሚገኙት ሀድያዎች የቀድሞው ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ሀረር ቢራ፣ኢትዮጲያ ቡና፣ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ፣አርባምንጭ ከተማ ና ወልዋሎ አሰልጣኝ ፀጋይ ኪዳነማርያም ሀድያ ሆሳእናን በአንድ ዓመት ውል ሊቀላቀል ችሏል።9 ነጥብ ይዞ በሊጉ መጨረሻ ደረጃ ሚገኙትን ሀድያዎችን የተረከቡት ፀጋይ ኪዳነ ማርያም አዲሱ ክለባቸውን ከወራጅነት አደጋ ነፃ የማድረግ ከፍተኛ ሀላፊነት ሚጠብቃቸው ይሆናል።

Hatricksport website writer

Twitter

ዳዊት ብርሀነ

Hatricksport website writer