ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ዛሬ በገበያ ላይ አለመዋሏን ተከትሎ በርካታ አንባቢዎቿ ወደ ዝግጅት ክፍላችንና በግልም ወደ አዘጋጆቹ ስልክ በመደወል ጋዜጣዋ ያልወጣችበትን ምክንያት ለማወቅ ጥረትን ያደረጉ ሲሆን ለእነዚሁ ሁሉ አንባቢዎቻችን በስልክ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ሆኖብናል፤ ስለሆነም ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ዛሬ በገበያ ላይ ያልዋለችው ትናንት ሰኞ በበዓል ምክንያት የስራ ቀን ባለመሆኑና ማተሚያ ቤታችንም ዝግ ስለነበር ጋዜጣው ሊታተምልን አልቻለም፡፡ ከአንባቢዎቻችን በቀረበልን ተደጋጋሚ ጥያቄ ምክንያት ጋዜጣዋ ነገ /ረቡዕ/ በገበያ ላይ እንድትውል ከፍተኛ ጥረት ብናደርግም በመብራት መጥፋት ምክንያት የማተሚያ ቤት ችግር ሊቀረፍልን ባለመቻሉ አሁንም ከአንባቢዎቻችን ጋር ለመገናኘት ያደረግነው ጥረት ሊሳካልን አልቻለም፤ በመሆኑም በተፈጠረው ችግር አንባቢዎቻችንን ይቅርታ እየጠየቅን አንባቢዎቻችን በእኔነትና በተቆርቋሪነት መንፈስ ጋዜጣው ለምን አልወጣም ብላችሁ ስልክ ደውላችሁ ለጠየቃችሁን በሙሉ እያመሰገንን በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ካልተሰሙ አዳዲስ ዘገባዎችና አነጋጋሪ ቃለ-ምልልሶች ጋር ቀናችንን ጠብቀን እንደምንገናኝ በእዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡

የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤዲቶሪያል ቦርድ
አስተያየት ይስጡ