(Exclusive በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት)
የኢትዮጵያ ፕሪምየር
ሊግ የቅርብ ጊዜ
የውድድር ተሳትፎ አቸው ላይ
በወጣትነት የዕድሜ ክልሉ
ላይ በመገኘት ለቡድናቸው
በቋሚ ተሰላ ፊነት በመጫወት
ከፍተኛ አድናቆትን ካተረፉ
ተጨ ዋቾች መካከል አንዱ
የሆነውና በቅርቡም
ለአልባ ኒያው ኬ.ኤፍ
ሴከንደርቢዩ ኮርሲ
ክለብ ለመጫወት
የሶስት ዓመታት
ፊርማውን ለማኖር
የቻለው የኢትዮጵያ
ንግድ ባንኩ የአማ
ካይ ስፍራ ተጨዋች
ቢኒያም በላይ
በክለቡ የሶስት ዓመ
ታት ቆይታው
ጥሩና ስኬታማ
ጊዜን ለማሳለፍ
መዘጋጀቱን እየተናገረ ሲሆን ከእሱም
በተጨማሪ ቡድኑ በሚጫወትበት የአውሮፓ
ሊግ ውድድር ላይ በቋሚ ተሰላፊነት ገብቶ
ለመጫወትና የሀገሩን ስም ለማስጠራትም
እንደሚፈልግ በተለይ ለሀትሪክ ስፖርት
ጋዜጣ እና ድህረ-ገፅ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያዊው ቢኒያም በላይ የአውሮፓ
ሊግ ላይ ለሚሳተፈው ክለቡ ፊርማውን ካኖረ
በኋላ የአሁን ሰዓት ላይ ከፍተኛ የደስታ
ስሜት እየተሰማው ሲሆን የተጨዋቹን ለክለቡ
መፈረምም በማወቅ ክለቡ በሚሳተፍበት
የአውሮፓ ሊግ ላይ ቢኒያምን ሲጫወት
ማየትም ብዙዎቹን የስፖርት ቤተሰቦች
ከወዲሁም እያጓጓ ይገኛል፤ ቢኒያም በላይ ወደ
አልባኒያ ተጉዞ የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ሙከራን ከማድረጉ በፊት አስቀድሞ የተጓዘው
ወደ ጀርመኖቹ ዳይናሞ ድረስደንና አዜንበርገር
እንደዚሁም ደግሞ ወደ ኦስትሪያም በመጓዝ
ለሬድ ቡል ሳልዝበርግ መጋቢ ክለብ ለሆነው
ኤፍሲ ላይፈሪንግ ሙከራ አድርጎ ለመጫወት
ቢሆንም ተጨዋቹ ለቡድኖቹ ሊመረጥና
ሊፈርም ስላልቻለም ነው በመጨረሻ
የአልባኒያው ክለብ ንብረት ሊሆን የቻለው፡፡
የድሬዳዋ ክልል ላይ ተወልዶ ያደገው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ቡድን የአማካይ ስፍራ ተጨዋች የነበረው
ቢኒያም በላይ የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ዕድሉን ለአልባኒያው ክለብ በመፈረም ካሳካ
በኋላ በቅርቡ ከዳይናሞ ዛግሬብ ጋር ተደርጎ
በነበረው የኤሮፓ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ
ጨዋታ ላይ ለቡድኑ በተጠባባቂ ወንበር ላይ
ተቀምጦ የታየ ሲሆን ተጨዋቹ በቀጣይ ጊዜ
ደግሞ ለቡድኑ ተሰልፎ ለመጫወት ጠንክሮም
እንደሚሰራ እየተናገረ ይገኛል፡፡
የቢኒያም በላይ ክለብ የሆነው ኬ.ኤፍ
ሴከንደርቢዩ ኮርሲ የአውሮፓ ሊግ የምድብ
ድልድል ውስጥ ከገባ በኋላ የአሁን ሰዓት
ላይ ከዩክሬኑ ዳይናሞ ኬቭ፣ ከስዊዘርላንዱ
ያንግ ቦይስና ከሰርቢያው ክለብ ፓርቲዚያን
ቤልግሬድ ክለቦች ጋር የተደለደለ ሲሆን
ቡድኑ የመጀመሪያውን ጨዋታም ከዳይናሞ
ኬቭ ጋር በመጪው ሳምንት ሐሙስ
ያደርጋል፤ የአልባኒያውን ክለብ የተቀላቀለው
ቢኒያም በላይ ለቡድኑ ፊርማውን ካኖረ በኋላ
በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ስላገኘው እድልና
ተያያዥ በሆኑ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነው
ምላሹን ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡
ሀትሪክ፡- ለአልባኒያው ኬ.ኤፍ
ሴከንደርቢዩ ኮርሲ ክለብ ለመጫወት
የተሰጠህን የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
የሙከራ ጊዜ በማለፍ የቡድኑ ተጨዋች
ሆነሃል፤ በመጀመሪያ እንኳን ደስ አለህ?
ቢኒያም፡- አመሰግናለሁ፤ ለእናንተም
ያገኘሁት ዕድል የጋራና ለሀገርም የሚጠቅም
ስለሆነ እንኳን አብሮ ደስ አላችሁ ለማለት
እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የአውሮፓ ሊግ ላይ
ለሚወዳደረው ክለብህ በቅርቡ ፊርማህን
ስታኖር ምን አይነት ስሜት ነው የተሰማህ?
ቢኒያም፡- የአውሮፓው ሊግ ላይ ለአዲሱ
ክለቤ ለመጫወት ፊርማዬን በቅርቡ ሳኖር
በውስጤ የተሰማኝ የደስታ ስሜት በጣም ከፍ
ያለ ነበር፤ ለቡድኑ ከመፈረሜ ባሻገርም ክለቡ
በነበረበት የአውሮፓ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ
ውድድር ላይም በተጠባባቂ ወንበር ላይ
የመቀመጥ ዕድልን
ስላገኘውና በእዚህ
ደግሞ ብቸኛውም
ኢትዮጵያዊ ተጨ
ዋች ስለሆንኩም
የደስታዬ ስሜት
እጥፍ ድርብ ሊሆን
ልኝ ችሏል፡፡
ሀትሪክ፡- ለፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ዕድሉ ወደ አልባኒያ ከመጓዝህ በፊት
ወደ ጀርመንና ኦስትሪያም አምርተህ
ሙከራን ማድረግህ ይታወቃል፤ እዚያ
ግን ሳይሳካልህ ቀረ ለምን ነበር?
ቢኒያም፡- የጀርመንና የኦስትሪያ
ሀገራት የሙከራ ቆይታዬ ላይ ለዳይናሞ
ድረስደን፣ ለአዜንበርገርና ለሬድ ቡል
ሳልዝበርግ ክለቦች ውስጥ ለመጫወት
ያደረግኩትን የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
የሙከራ ዕድል ምንም እንኳን ሳይሳካልኝ
ቀርቶ ለክለቦቹ ፊርማዬን ለማኖር
ባልችልም ወደ ቡድኖቹ ያልገባሁበትን
መንገድ አሁንም ድረስ ግን እኔ
አላወቅኩትም፤ በሙከራ ጊዜ እድሉ እንደ
እኔ እምነት ጎሎችን ከማስቆጠሬ ባሻገር
ስራዬን በአግባቡ ሰርቼና ጥሩ ጊዜን
እንዳሳለፍኩ አውቃለው፤ እኔን መያዝና
አለመያዝ ደግሞ የእነሱም ስራ ነውና
በእዚሁ ምክንያት ወደ ክለቦቹ ሳልገባ
ቀርቻለው፤ በመጨረሻ ግን ፈጣሪዬ ለእኔ
ያሰበውና የተሻለም ነገር ስለነበር ኤሮፓ
ሊግ ላይ ለሚወዳደረው የአልባኒያው
ቡድን በማምራትና ሙከራውን በማለፍ
ለቡድኑ ልፈርም በቅቻለው፡፡
ሀትሪክ፡- የአልባኒያው ክለብ ውስጥ
ፊርማህን ስታኖር ለምን ያህል ዓመት
ለመጫወት ነው፤ ክለብህ የሚከፍልልህ
ወርሃዊ ደምወዝና ሌሎች እያደረገልህ
ያለው ነገርስ ምንድን ነው?
ቢኒያም፡- የዝውውር መስኮቱ
ላይ ለክለቤ ኬ.ኤፍ ሴከንደርቢዩ ኮርሲ
ለመጫወት በቅርቡ ፊርማዬን ያኖርኩት
ለ3 ዓመታት ቡድኑ ውስጥ ለመቆየት
ነው፡፡ የወርኃዊ ደምወዜን በተመለከተ
የገንዘቡን መጠን አሁን ላይ መናገር
አልፈልግም፤ ክለቡ ሌሎች የሚያደርግልኝ
ነገር የምኖርበትን አፓርታማ አዘጋጅቶልኝ
እዚያ እየኖርኩ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የክለባችሁ ኬ.ኤፍ
ሴከንደርቢዩ ኮርሲ የፕሪ ሲዝን ዝግጅት
ምን ይመስላል? በክለቡ ያለው አጠቃላይ
የቡድን መንፈስስ ምን ይመስላል…
ቢኒያም፡- የአውሮፓ ሊግ ላይም
ሆነ ሴፕቴምበር 9 ለሚጀመረው
የአልባኒያ ሱፐር ሊግ ውድድር እየተዘጋጀ
የሚገኘው ጠንካራው ክለባችን ለዘንድሮ
የውድድር ተሳትፎው ከወዲሁ እያደረገ
ያለው የፕሪ ሲዝን ዝግጅት በጣም ጥሩ
የሚባል ነው፤ በቅርቡ ያደረገውን የኤሮፓ
ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታን አሸንፎ
ወደ ምድብ ድልድሉ መግባቱ ቡድኑን
በከፍተኛ ሁኔታ እንዲነቃቃ አድርጎታል፤
ያ ተደናቂ ውጤትም አጠቃላይ የቡድኑ
ተጨዋቾችንም በውጤቱ እንድንደሰትም
አድርጎናልና ያለው መንፈስ ጥሩ
የሚባል ነው፤ ቡድናችን በእዚህ ደረጃ
ላይ መገኘቱም ቀጣይ በምናደርጋቸው
ውድድሮችም ላይ ሁላችንም የቡድኑ
ተጨዋቾች ጥሩ ውጤት ለክለባችን
ለማምጣትም ስለሚያስችለን ጠንክረን
ልምምዳችንንም እየሰራን ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የእናንተ ክለብ ውስጥ
ከአንተ ውጪ የምን የምን አገራት ዜጎች
አሉ?
ቢኒያም፡- የኬ.ኤፍ ሴከንደርቢዩ ኮርሲ
ክለብ ውስጥ የአሁን ሰአት
ላይ ከእኔ ውጪ የሚገኙት
የውጪ ሀገር ተጨዋቾች
የብራዚል፣ የግሪክ፣ የጣሊ
ያን፣ የቤልጅየም፣ የአልባኒያ፣
የናይጄሪያ፣ የጋምቢያ፣ የኬፕ
ቬርዴና የመሳሰሉት አገራት
ዜጋ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
ሀትሪክ፡- የአልባኒያው
ክለብ የ3 አመታት ቆይታ ላይ
ከወዲሁ ምን አይነት ቆይታና
የውድድር ጊዜን አሳልፋለሁ
ብለህ እያሰብክ ነው?
ቢኒያም፡- ለአልባኒያው
ክለብ ፊርማዬን ካኖርኩበት
ጊዜ አንስቶ በክለቡ የተሳካ
የሚባል የጨዋታ ጊዜን
ለማሳለፍ ከወዲሁ በሁሉም
መልኩ እየተዘጋጀው ነው፤
የመጀመሪያ ዓመት ቆይታዬም ላይ
ከቡድኑ ጋር በሚገባ ለመዋሀድ በግሌና
ከቡድኔ ጋር ጠንካራ የሚባሉ ልምምዶችን
በመስራት ቡድኑን በደንብ መላመድ
እፈልጋለው፤ ከአሁን ጀምሮም በተከታታይ
ዓመት ቆይታዬ ላይ ለክለቡ በቋሚ
ተሰላፊነት ለመጫወትም የተቻለኝን ሁሉ
ጥረት ማድረግ እፈልጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- የፕሮፌሽናል ተጨዋች
ከሆንክ በኋላ እዚያ ባሉት ሁኔታዎች ምን
የተለየ ነገርን ተመለከትክ?
ቢኒያም፡- የፕሮፌሽናል ተጨዋች
ሆኜ አልባኒያ ከመጣሁ በኋላ እኛ
አገር ላይ ካለንበት ሁኔታ አንፃር እዚያ
የተመለከትኩት ነገር ቢኖር በብዙ ነገር
እንደምንለያይ ነው፤ አጠቃላይ ሁኔታውን
በቀላሉ ለመግለፅም ሁሉም ነገር ቀላል
የሚሆንም አይደለም፡፡
ሀትሪክ፡- ለፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ደረጃ ለመድረስህና የምታመሰግነው ሰው
አለ?
ቢኒያም፡- የአውሮፓ ሊግ ላይ
ለሚወዳደረው ክለቤ ፊርማዬን እንዳኖርና
በቀጣይም ለክለቡ ለመጫወት እንድችል
የማመሰግነው አካል ቢኖር በመጀመሪያ
ፈጣሪዬን ነው፤ በመቀጠል ደግሞ ለእኔ
የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እድሉን
ያመቻቹልኝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ
ፌዴሬሽን የቴክኒክ አማካሪ የሆኑት
ጀርመናዊው ሚ/ር ጆአኪም ፊከርትን፤
የብሄራዊ ቡድን ላይ የመረጠኝን አሰልጣኝ
ዮሃንስ ሳህሌን፤ ከልጅነቴ አንስቶ ለብዙ
አመታት እንደ አባትና ወንድም ሆኖ
ያሰለጠነኝንና ያሳደገኝን አሰልጣኝ እዮብ
ተዋበን፣ ቤተሰቦቼንና ፍቅረኛዬን
እንደዚሁም ደግሞ የቀድሞ ክለቤን ባንክና
የክለቡን አመራሮች በጣም ማመስገን
እፈልጋለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
ላይ በድጋሚ ተጠርተህ ለመጫወት ያለህ
ፍላጎት የት ድረስ ነው?
ቢኒያም፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
ውስጥ ዳግም ተመርጬ የመጫወት
ፍላጎቱ ቢኖረኝም አሁን ላይ እድሉን
ለማግኘት እኔ ፈጣሪ ያውቃል ነው
የምለው፤ ለሀገሬ ለመጫወትም ጊዜ
ሲደርስ የምወስነው ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የአልባኒያው ክለብ ውስጥ
ለመጫወት ስንት ቁጥር ተሰጠህ?
ቢኒያም፡- የአልባኒያው ክለብ ውስጥ
ፊርማዬን ሳኖር ለእኔ የተሰጠኝ የማልያ
ቁጥር 18 ነው፤ የመሰለፍ እድሉን ሳገኝ
ያንን ለብሼ እጫወታለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- አሳዳጊክ የኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ ክለብ ከሊጉ ሲወርድ ምን ተሰማህ..
እንዴትስ ልትወርዱ ቻለችሁ?
ቢኒያም፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር
ሊግ ላይ ለበርካታ አመታት ቆይቶ
የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ
ለመጀመሪያ ጊዜ በእኔ የተጨዋችነት
ዘመን ወደታችኛው ዲቪዝዮን ሲወርድ
በክለቡ ውስጥ ከመቆየቴ አኳያ በጣም
አዝኛለሁ፤ ቡድናችን የወረደበት ሁኔታን
በተመለከተ ግን ዛሬ ላይ ምንም ነገርን
ማለት አልፈልግም ስለዚህ ጥያቄው
ቢያልፈኝ ጥሩ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ክለብ ዳግም ከወረደበት በመምጣት
የፕሪምየር ሊጉን ይቀላቀላል?
ቢኒያም፡- አዎን፤ ቡድኑ ጥሩ አቅም
ስላለው ከፈጣሪ እርዳታ ጋር የአጭር ጊዜ
ውስጥ ወደፕሪምየር ሊጉ ይመለሳል፡፡